አርቲስቶቹ የህወሐት 40ኛ ዓመት ይደገም ቢሉስ?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ኤልያስ (አዲስ አድማስ)

ሁሌም ምርጫ ሲደርስ ብቅ ብቅ የሚሉ (በኢቢሲ ማለቴ ነው!) ፊታቸው “የቁጣ አስተማሪ” የሚመስል አንዳንድ ግለሰቦች አላጋጠማችሁም? ፖለቲከኞች ወይም ባለሥልጣናት እንዳይመስሏችሁ። (እነሱ አይቆጡም አልወጣኝም!) እነዚህኞቹን “የምርጫ ዬኔታ” ይሏቸዋል፡፡ ይሄ ስያሜ ለምን እንደተሰጣቸው አላውቅም፡፡ ምናልባት ቁጣ ቁጣ ስለሚላቸው ይሆን? የሚገርመው ደግሞ እየተቆጡ የሚያስተምሩን እንዴት ምርጫውን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ---እንደምናደርገው ነው፡፡ (ሰላማዊ ምርጫ --- በቁጣ?!)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesusክንፉ አሰፋ

አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ። መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት።

"ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው። ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!"

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዶርዜ ማርያም

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

 አስፋ ጫቦ

1. ዶርዜ ዴሬ (አገር) የዶርዜ ማርያም የለችም። ያሉ ሁለቱ አድባራት የጥንቱ፣ የጥዋቱ የዶርዜ ጊዮርጊስና የዶርዜ ሚካኤል ናቸው። ሚካኤል ከጨንቻ በልጅ እግር ከ30-45 ደቂቃ ቢወስድ ነው። በምን ሊከድ ኖሯል!? ልጅ ሆኜ አንድ ሁለቴ ሚካኤልን ለማንገስ መሔዴ ትዝ ይለኞል። ማንገሱ ሳይሆን የዶርዜ ዘፈኑ መስለኝ የሚጠራኝ። ታላቅ የሙዚቃ ትዕይንትና ቲያትር አደራሽ እንደመግባት ይሰማኛል። አዳራሹ ሜዳው መሆኑ ነው። ዶርዜ ማርያም ብትኖርም እንኳ ዶርዜ ማራሞ ነው የምንለው። ታሪካዊዋንን የዜናሁ ለጋለ፤ የአባ ባሕርይ መጽሐፍ መፍለቂያ የብርብር ማርያም ደብረ ነች። ያችን እኛ ቢርቢራ ማራሞ እንላለን። ዚኒ ከማሁ፤ ኤሌ ጋብሬሌ፤ ዶርዜ ሚካሌ ነው የምንለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት እና መኢአድ ነገር ቀላል አስቆዘመኝ እንዴ... ቁጭት እንደወረደ!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

 ኣቤ ቶክቻው

በተለይ አንደነት ፓርቲ በበኩሌ ቀልቤን የሳበው ሲመሰረት ጀምሮ ነበር። ”የቅንጅት ህጋዊ እና ሞራላዊ ወራሾች ነን!” የምትለው ንግግር ዋዛ አልነበረችም። በብዙነታችን ውስጥ አንድነት የሚለው ሃሳብ ለሀገሬ መልካሙ መንገድ ነው ብዬ ስለማስብ ይሁን፣ የብርቱካን ሚዴቅሳ እና ፕሮፌሰር መስፍን ፖለቲካዊ ስብዕና ደስ ስለሚለኝ ይሁን፣ እነ አርአያን የመሳሰሉ ወዳጆቼ በዙሪያው ስለነበሩ ይሁን ብቻ በቅጡ ባለየሁት ሁኔታ በልቤ አንድነት ፓርቲ ክፉ ባይነካው ብዬ ስጸልይለት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምክር እስከመቃብር – ከኣልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ (በእውቀቱ ሥዩም)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

በእውቀቱ ሥዩም

የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር እየመጣሁ ነው። ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው።እናቶች ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን እንዳትጀምሩት ኣደራ። ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ። የጥይት መከላከያ ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ። ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ እቆጣጠራለሁ። በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ። ባሩድ ኣገነፋለሁ። የታንክ ጎማ እነፋለሁ። በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤ በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስ “ትሩፋቶች” (ባለቤት አልባ ከተማ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ደራሲ:- ኤርምያስ ለገሰ
ቅኝት:- መስፍን ማሞ ተሰማ

መንደርደሪያ
በድሮ ዘመን የኖሩ እንስሳት እንዲህ ዘመሩ።
የእንግሊዝ አራዊት፤
የአየርላንድ አራዊት፤
የየሀገሩ ሁሉ አራዊት፤
ተሳተፉ የደስታዬን ምንጩን፤
ስለመጪው ብሩህ ዘመን!
ይዘገያል ወይ ይፈጥናል፤
ያ! ቀን ግን ይመጣል፤
ጨቋኙ ሰው ይገረሰሳል! . . . ዘምረው ዝም አላሉም። ዘምረው አመፁ። አብዮት አፈነዱ፤ የእንስሳት አብዮት። በሚኖሩበት ሀገር - በእነሱ አጠራር፤ የእርሻ ጣቢያ - ለዘመናት በጭቆና ቀንበር ረግጦ ሲገዛቸውና ሲመዘብራቸው በኖረው የሰው ዘር ገዢያቸውና ግብረ አበሮቹ ላይ ሆ! ብለው ተነሱ። ቀንበር በቃን። ባርነት በቃን። ብዝበዛ በቃን። … ነፃነት እንጂ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ