ስለሚልዮን ሹሩቤ (በሰናይ ቸርነት)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

የምሰራበትን የሚዲያ ተቋም ወክዬ በተለያዩ የፕሬስ መግለጫዎች ላይ እካፈል ነበር፡፡ በዚህም አጋጣሚ ከተለያዩ ነባርና አዳዲስ የሙያ አጋሮቼ ጋር የመተዋወቅ ዕድሉ አጋጥሞኛል፡፡ ከጋዜጠኛ ሚልዮን ሹርቤ (የማራኪ መጽሔት ባለቤት) ጋር ግን እንደሌሎቹ ተቀራርቤ ባልግባባውም በተገናኘኝ ቁጥር የአንገት ሠላምታ ከመስጠት አልቦዘንኩም፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መልዕክት (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

‹‹ለእስረኛ ማልቀስ/ ማዘን ሳይሆን የእስረኛውን መንገድ መከተል ነው››

‹‹የእስክንድር ሃሳብ ትክክል ነው›› ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከነገረን የተወሰደ

‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ በተስተናገዱ ሶስት ጽሑፎች ተከስሶ ለሁለት ዓመት ያህል የክስ ሂደቱ ሲታይ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ‹‹ጥፋተኛ›› ከተባለ በኋላ ከትናንት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዛሬ ጥዋት ላይ ከእስከዳር አለሙ፣ ይድነቃቸው ከበደ እና ስለሺ ሀጎስ ጋር ሄደን ጠይቀነው ነበር፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

''አታምጣው ስለው አምጥቶ ቆለለው!''

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አቤ ቶክቻው

ትላንት ለንደን ነበርኩ። እኔ ካለሁበት ማንችስተር ከተማ ለንደን ለመሄድ ወደ ስምንት መቶ ሰው ጭኖ በሰዓት እስከ ሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ድረስ በሚወነጨፈው ቨርጂን ባቡር የፈጀውን ይፍጅ ብዬ ከተሳፈርኩ ሁለት ሰአት ከ ሃያ ደቂቃ ብቻ ነው የሚወስድብኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን “የስጋት” መስመር (ከዞን9 ጦማሪያን)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ይህ አመት አንደተለመደው አይነት አመት ቢሆን ኖሮ በዚህ ወቅት የዞን9 ጦማርያን በጦማሪት ማህሌት አስተባባሪነት፣ በአጥናፍ ብርሃኔ እና በጆማኔክስ ካሳዬ ትብብር የአመቱን ታላላቅ ክስተቶች አሰባስበው ከመታተሙ በፊት ለቡድኑ ክለሳ የሚያቀርቡበትና የተረሱ እና ለክስተትነት የማይበቁ የምንላቸውን ሁነቶች የምንለይበትና የአመቱን የጊዜ መስመር የምናወጣበት ወቅት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከታሳሪ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪና አህመዲን ጀበል ጋር በቂሊንጦ የነበረኝ ቆያታ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ
"እኛ ታስረንም፣ በኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት እና ጋዜጠኞች ላይ የሆነው ነገር እጅግ ቅስም ይሰብራል (It's really heart breaking!)" ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ
"እስር ደግም ነገር ነው" ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
"የነጻነት ትግል ላይ እንዳለሁ ያወኩት እስር ቤት ነው" ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ
"መጽሔቶች መታተም መቆማቸው ያሳዝናል፣ አማራጩ ምን ይሆን?" አህመዲን ጀበል (የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል)

ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በጣም የናፈቁኝን ታሳሪ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ለመጠየቅ በማቀድ፣ ረፋድ ላይ ወደቂሊንጦ እስር ቤት አመራሁ። በቃሊቲ ወህኒ ቤት ዋና በር ጋር በታክሲ ሳልፍ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እና ኤዶምን ካሳዬ፣ ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁንን፣ አቶ አንዷለም አራጌን፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና ሌሎች የማውቃቸውን እስረኞች በሀሳቤ መጥተው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ” በፍቃዱ ኃይሉ ከቂሊንጦ እስር ቤት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Befekadu Hailu Zone 9 Blogger በፍቃዱ ኃይሉ (የዞን 9 ብሎገር ከቂሊንጦ እስር ቤት)በፍቃዱ ኃይሉ (የዞን 9 ብሎገር ከቂሊንጦ እስር ቤት)

”ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!”፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ። በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ”አባሪዎቼ” ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ  ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ