‹‹… ያኔ በምወደው የጋዜጠኝነት ሙያ እየሰራሁ እቀጥላለሁ››

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ (ከቃሊቲ እስር ቤት)

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ

ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ከታች በፎቶግራፍ የምንታይ [ፎቶግራፉን ያነሳው አብነት ረጋሳን ጨምሮ] ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ“pen Golden of freedom 2014″ ተሻላሚ በመሆኑ ‹‹እንኳን ደስ ያለህ›› ለማለት ኬክ አስጋግረን ወደቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡ቁጥራችን መብዛቱ በቃሊቲ ያሉ ፖሊሶችን ግር ማሰኘቱ አልቀረም ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መልካም የእናቶች ቀን

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ(የልጆቻችሁ እስር አንጀታችሁን ላሳሰራችሁ)

ጽዮን ግርማ

እኔና ጓደኛዬ (ሊሊ) የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ)ን ደጅ የረገጥነው በጠዋት ነበር። ምግብ ማቀበል እንጂ ማግኘት ስለማይቻል የግቢው በር እንደተከፈተ ለልብ ወዳጃችን የወሰድነውን ቁርስ ሰጥተን ያደረ ተመላሽ ዕቃ እስኪመጣልን ከመግቢያው ፊት ለፊት ባለው ድንጋይ ላይ ቁጭ ቁጭ ብለናል።ቀዝቀዝ ባለው አየር ላይ ጥቂት ካፊያ ስለነበር ቅዝቃዜው ኩርምት አድርጎናል። ጥቂት ቆይቶ አንዲት እናት በስስ ፌስታል አንድ አራት የሚኾን ፓስቲ (ቤት ውስጥ የሚጠበስ ቂጣ መሰል ብስኩት) ጠቅለል አድርገው ይዘው ወደኛ መጡ ፊታቸውን ጭንቅ ብሎታል። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የስቅለቱ እና የትንሣኤው አብነት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ስቅለትከሆሳዕና እስከ ማዕዶት

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል ተከብሮ የሚውለው፣ በዕለተ እሑድ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በዕለተ እሑድ-መጋቢት 29 ቀን ነው። የግዕዝ ቋንቋ ሊቃውንት እንደሚተረጉሙት ከሆነ፣ “ትንሣኤ ማለት-መነሳት ማለት ነው።” ሞትን ድል አድርጎ፣ ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው። “ሕይወት ማግኘት፣ ነፍስ መዝራት፣ ሕልው መሆን” ማለት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ሰርከስ መስራች በሳውዲው ስደት

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

አስገራሚው የሳውዲው "ኮራጅ " አባት ምክር

ነቢዩ ሲራክ
ነገሩ እንዲህ ነው፤ ከ20 ዓመት በፊት ሳውዲው ወጣት ራሱን ለሁለተኛ ደረጃ ፈተና ከማዘጋጀት ይልቅ በረቀቀ መንገድ ለፈተናው መልስ የሚሆነውን ማጭበርበሪያ የመልስ ወረቀት አዘጋጅቶ ለፈተና ይቀርባል። ፈተናውን በረቀቀ መንገድ አጭበረብሮ ሰርቶታልና ፈተናውን በተገቢ ውጤት አልፎ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለማለፍ በቃ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማለዳ ወግ፤ የመረጃዎች እውነት - ሐሰት ፍልሚያ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Ethiopians in Saudiየተመላሾች ጉዳይ ...
ነቢዩ ሲራክ
ከሳውዲ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ዜጎችን በሚመለከት የጀርመንና የአሜሪካ ራዲዮን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙኀን አንድ አይነት የሚመስል መረጃ ግፉአን ተመላሾችን እማኝ እያደረጉ መረጃ አቀብለውናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ሄኖክ የሺጥላ

"አወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ
ብቸኛው ልቤ ሰው በመውደዴ"

ነው ያለው አረጋሃኝ ወራሽ አሁን እንደሱ ልፋትና ጥረት ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የት በደረሰ። ለነገሩ ይሄ ትውልድ የተሠራውን ሁሉ በመናድ፣ የተጣፈውን ሁሉ በመካድ ነው የሚታወቀው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ