የጠለፋ ጋብቻ በኢትዮጵያ፡ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ወንጀል

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም- በነጻነት ለሀገሬ)

እውነታው ከልብወለድ በላይ እንግዳ ነገር ነው!

እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 7/2014 “ድፍረት፡ የፊልም ጠለፋ በኢትዮጵያ ” በሚል ርዕስ ባወጣሁት ትችት ድፍረት በሚለው ፊልም ላይ የኢትዮጵያ መሪ ተዋንያን ሆና በሰራችው የውርጃ ድርጊት ላይ የነበረኝን ቁጣ ገልጨ ነበር፡፡ በአበራሽ በቀለ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው ያ ፊልም በአሁኑ ጊዜ ጠለፋ እየተባለ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለአቅመ አዳም ባልደረሱ ልጃገረዶች ላይ የሚፈጸመውን እውነተኛ ኢሰብአዊ እና ኋላቀር ልምድ በማጋላጥ እየተሰራ ያለውን የትወና ታሪክ ይተርክልናል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማለዳ ወግ … በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ / ደ.ህ.ዴ.ን ክብረ በዓል

ነቢዩ ሲራክ

በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ክንፍ የደ.ህ.ዴ.ን ፖለቲካ ፖርቲ አባላት ወዳጆቸ ባደረጉልኝ ግብዣ መሰረት በደ.ህ.ዴ.ንን 22ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተገኝቸ ነበር። እንደ ዛሬው የደ.ህ.ዴ.ን በዓል ፍሪዳ ተጥሎ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ድርጅቶች የልደት በዓላቸውን ሲያከብሩ እግር ጥሎኝ ስገኝ በምባረርበት የጅዳ ቆንስል ግቢ በሚገኘው የኮሚኒቲ አዳራሽ ተገኝቸም ኬክ እስኪቆረስና ሙዚቃው እስኪጀመር ያለውን ፕሮግራም ተከታትያለሁ። በልደት ፕሮግራሙ በቀረበው የድርጅቱ የትግልጉዞ “የስምጥ ሸለቆው ታጋዮች” የሚል ስያሜ የተሰጠውን የደቡብ የነጻነት ታጋዮች ከህወሃት ጋር ተቀዳጅተው በቅድመ ደርግ ያደረጉትን ትግል ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር የሰማሁት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕሮፌሰር መስፍንን ለቀቅ

ጋዜጠኛ አንተነህ መርዕድ

በዙህ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ በሁለት ምክንያቶች ከራሴ ጋር ብዙ ታግያለሁ። መጀመርያ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አይደለም ለራሳቸው፤ ለሌላም የሚተርፍ አንደበት አላቸውና ራሳቸው መልስ ይስጡ በማለት ሲሆን ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ ትልልቅ አገራዊ ጉዳይ እያለ በዚህ ጠባብ ነገር መጠመድ ለማን ይበጃል በሚል ነበር።በሁለቱም ትክክል አልነበርሁም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወዳጃችን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ወዳጃችን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ከተከሰሰባቸው ክሶች በአንደኛው ሶስት አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት

አቤ ቶኪቻው

በሌሎቹ ክሶች ምን እንደሚፈረድበት ቀጥሎ የምናየው ቢሆንም ተሜ እና ሌሎች ወንጀለኛ ያልሆኑ ሰዎችን … (ይሄን ግዜ አንዳድ አብዝተው የዋህ የሆኑ ሰዎች እና አብዝተው የኢህአዴግ ዝምድናን የተጋመዱ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ወንጀለኛ ያላቸውን ሰዎች ከወንጀል ነጻ ናቸው ማለት ተገቢ ነውን… እያሉ ሊሞግቱን ጣታቸውን ሲያሞጠሙጡ ይታየኛል …

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማለዳ ወግ ... ይድረስ ለወዳጀ ወንድም ለወዳጀ ታሪኩ ደሳለኝ!

ነቢዩ ሲራክ

ወንድሜ ሆይ ማምሻውን ”… አሁን የማወራው ስለ ብትቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋ እና ርህሩዋ እናታችን ነው!” በማለት ስለ እናትህ ጭንቀት የጻፍከውን ሳነበው፣ ስለ እናትህ ልቤ በሃዘን ተጎዳ፣ ስለ ጀግኖች ሳይሆን ስለ ጀግና እናቶች መከራ አነባሁ፣ እንደ ሰው በእልህ ሰውነቴ ጋለ፣ ተናደድኩ … በቁጭት ግን አልቆዘምኩም …!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መክሸፍ እንደ እኔ ጉብኝት

ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ዓለማየሁ ገላጋይ

የጉብኝት ጉዞው በማለት ተጀምሯል፤ ያለንበት መኪና ወደ አዲስ አበባ ደቡብ አፍንጫውን ቀስሯል፤ በመካከላችን ጸጥታ ረብቧል … ዕጣ ፈንታህ በዘመን እጅ ነው ዘመን ሲፈቅድ የዘመንህ ‹‹ጉዱ ካሳ›› ትሆናለህ፤ ስውር እስር ቤት ትገባለህ፤ እንደ እብድ ትታያለህ፤ በመገለል ዘብጥያ ባመደመጥ ዋርድያ ስር ትሆናለህ፡፡ እውነትህ እንደቅራቅንቦ ይቆጠራል ይናቃል …
… ወይም …

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሀብታሙ አያሌው ስለ "መለስ ራዕይ" ምን ብሎ ነበር?

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

‹መለስ በህይወት ቢኖር ራሱ የሚቃወማቸው ይመስለኛል››
‹‹አቶ ኃይለማርያም፣ የራሱን አመለካከት አሳድራለሁ ያለ ቀን፤ ወደ እነአንዱአለም ጎራ ይቀላቀላል፤ መለስ ቢኖርም ባይኖርም!!!›› አቶ ሀብታሙ አያሌው /የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ/

አሁን በእስር ላይ ማዕከላዊ ሆኖ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእግር ህመም እየተሰቃየ የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ አቶ ሀብታሙ አያሌው ከመታሰሩ 10 ቀናት ቀደም ብሎ ለ‹‹ቀዳሚ ገጽ›› ጋዜጣ እኔ እና ባልደረባዬ አናንያ ሶሪ በ‹‹መለስ ራዕይ›› ዙሪያ ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ አድርገንለት ነበር፡፡ ቃለ-ምልልሱም በጋዜጣው ላይ ተስተናግዷል፡፡ ቃለ-ምልልሱን ማንበብ ላልቻላችሁ ወገኖቼ ታነቡት ዘንድ የተወሰነውን እንዲህ አቅርቤዋለሁ፡-

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወያኔ ወሮበላ ዲፕሎማሲያዊነት

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም:- ነጻነት ለሀገሬ)

እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ወያኔ እያለ በሚጠራው እና ትግሉን በሰለጠነ መልኩ በጠረጴዛ ውይይት እና የሀሳብ የበላይነት ሳይሆን ከጫካ በመግባት ብረትን የኃያልነት ዋስትና በማድረግ በንጹሀን ዜጎች ደም ላይ ተረማምዶ የጫካ ባህሪውን ከነግሳንግሱ እንዳለ ተሸክሞ ከህዝቦች ፈቃድ ውጭ በኃይል በህዝቦች ጫንቃ ላይ ተፈናጥጦ በሚገኘው የሽፍታ ቡድን የበላይነት የሚመራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በአፍሪካ ወደር የማይገኝለት አምባገነን እና አረመኒያዊ ስብስብ እንደሆነ በተደጋጋሚ ስገልጽቆይቻለሁ። ዴሞክራሲ በህዝብ ለህዝብ የተቋቋመ ህዝባዊ አስተዳደር ከሆነ የወሮበላ አገዛዝ መንግስት ደግሞ በዘራፊዎች እና በወሮበላዎች ለዘራፊዎች እና ለወሮበላዎች የተቋቋመ የማፊያ ቡድን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምጽዓት

ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም

በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደኤርምያስ መጣ፡– ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፤ — የእሥራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤- እነሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል፤ በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም፤ ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በበእኔ ታምነሃልና ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 39/15-18

ኑዛዜ ኤርምያስን አነበብሁ፤ጉድ ነው! አንድ የማውቀውን ነገር አረጋግጥሁ፤ ብዙ የማላውቃቸው ነገሮችን አወቅሁ፤ የማውቀው ነገር ሂሳብ የተማረ ሰው ምን ጊዜም ጭፍን ሎሌ መሆን የማይችል መሆኑን ነው፤ሂሳብ የተማረውን ሰው ለጭፍን ሎሌነት የሚቀጥረው ሰው ግን አንጎሉ የፈረጠ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እስክንድር ነጋ ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ

"ተመስገን፣ ጥሩ ታጋይ እና ሰው ሆኖ ከእስር ይወጣል"
"ተመስገን፣ የህዝብ ልጅ ነው፤ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ"

እስክንድር ነጋ "ስለተመስገን ደሳለኝ ሃሳቤን አስተላልፍልኝ" ካለኝ የተወሰደ

ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ዕለት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆነውን አቶ አንዷለም አራጌን በ2007 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ላገኛቸው ችዬ ነበር – ለአቤል አለማየሁ ጋር። ባለፈው ሳምንት የ"ባንዲራ ቀን" በተከበረበት ዕለት ቃሊቲ ከወዳጄ እዩኤል ፍስሐ ጋር ሄጅ እነስክንድርን መጠየቅ ሳንችል ተመልሰን ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ