አዟሪና አከፋፋዮች ለምን አንድ ለአምስት አይደራጁም?

ጽዮን ግርማ

ከአምስት ወራት በፊት ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። በሞያው ውስጥ ሰንበት ብያለኹና ከአብዛኞቹ የጣቢያው ዘጋቢዎች ጋራ እንተዋወቃለን። ጥሪው የደረሰኝም በላይ ኃድጎ ከተባለ ከማውቀው ጋዜጠኛ ነበር። ለሥራ ጉዳይ በስልክ ሳይኾን በአካል መገናኘት እንደሚፈልግ ነገረኝ። ባለመመቻቸት ሳንገናኝ ቀናት ቢቆጠሩም በመጨረሻ ተገናኘን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአፍሪካ ነገር-የኢትዮጵያ ነገር

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

በሃያኛው ምዕተ-ዓመት ላይ የታወቀ የፈረንሳይ ፈላስፋ ነበረ፤ እሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ከእሱ ጋር በዩኒቨርሲቲ ሁለት አፍሪካውያን አብረውት ይማሩ እንደነበሩ ይናገራል፤ እነዚህ አፍሪካውያን የፈረንሳይኛ ቋንቋን ልክ አንደፈረንሳዮች እየተናገሩ፣ እንደፈረንሳዮች እያሰቡ ከፈረንሳዮቹ ተማሪዎች ጋር እኩል በትምህርት እየጎለበቱ ነበር፤ በኋላ እነዚህ አፍሪካውያን ወደአገራቸው ተመልሰው ሥልጣን ላይ ሲወጡ ሰፊ አገራቸው ለሁለቱ የተማሩ አፍሪካውያን የማይበቃ ሆነባቸው፤ ስለዚህም አንደኛው የአገር መሪ ሆነና ሌላውን ገደለው፤ የፈረንሳዩ ፈላስፋን ያሳዘነው ትዝብት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሀገር የኮምፒዩተር ቫይረስና ሀከር ነው እንዴ?

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ከዓመታት በፊት የቅንጅት አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት አባሎችና ሌሎች ሰዎች ተከሰው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ”የቅንጅት አመራሮች የፍርድ ቤት ውሎ” በሚል ርዕስ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ተከታታይ ዘገባ አቀርብ ስለነበር ችሎቱ እስኪጠናቀቅ አንድም ቀን ከፍርድ ቤት ቀርቼ አላውቅም ነበር። በዚህም የተነሳ ክሱና የክርክር ሂደቱ ምን እንደሚመስል መናገር የሚያስችል መረጃ አለኝ ለማለት እደፍራለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከእስሩም በላይ - “ሽብርተኝነት”

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

እስረኞቹ በሽብር መከሰሳቸውን አያውቁም
ጽዮን ግርማ

አንድ ዓመት ከአንድ ወር ኾኖታል። እስክንድር ነጋ ከታሰረ ከዐስራ ስምንት ወራት በኋላ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በሰኔ የመጀመሪያ ወር ላይ በ2005 ዓ.ም. እንደተፈቀደለት፤ እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ወደሚገኘው እስር ቤት አምርቼ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአዲስ አበባ የመሬት ቅርጫ

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

ዮሐንስ ታደሰ አካ የሚባል ወጣት ስደተኛ የተስፋው ነጸብራቅ የሚል መጽሐፍ እአአ በ2013 በጀርመን አገር አሳትሞአል፤ ሳይፈራ ሀሳቡን የሚገልጽ በመሆኑ ሳይሆን አይቀርም በታወቀው ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያና በቃሊቲም ታስሮ ነበር፤ እሱ እንደሚለው "በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የመሬት አስተዳደር ባለሥልጣን ውስጥ … የመሬት መሀንዲስ" ተብሎ በ2000 ዓ.ም. ተቀጠረ፤ ከተቀጠረ በኋላ በቦዘኔነት ደመወዝ እየበላ ቆየ፤ ቀይቶ እንደተገነዘበው "… ለካስ እንኳንስ የእያንዳንዱ ሠራተኛ የሥራ ድርሻ ተለይቶ ሊታወቅ የመሥሪያ ቤቱም ሥራ አይታወቅም፤ መሥሪያ ቤቱም ሥራውን አያውቅም፤ የመሥሪያ ቤቱም ሃላፊዎች መሥሪያ ቤቱን አያውቁትም፤ ጉድ በል አዲስ አበባ! የምናወራው ስለዝነኛው አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ነው።" (ገ. 19)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

‹‹ቀዩ መስመር›› የቱ ጋር ነው?

ጽዮን ግርማ (ጋዜጠኛ)

ኢትዮጵያ በፓርቲ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ባህል ውስጥ የገባችው የ1960ዎቹን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው። በዚህም ምክንያት የተለያዩ ርዮተ ዓለሞች ተፋጭተው ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ይመሰረትባታል በሚል ተስፋ ቢጣልም የድርጅቶቹ የኋላ ታሪክ እንደሚያስረዳው ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ለውጥ ከማምጣት ይልቅ እርስ በእርስ የመጨራረስ ባህል እንደነበራቸው ነው። ከበርካታ ንፁሃን ዜጎች ደም መፍሰስና እልቂት በኋላ ህወሓት ኢሕአዴግን መሥርቶ ወደ ሥልጣን ሲመጣም ከሻዕቢያ በስተቀር ሌሎቹ ድርጅቶች እስከ አመራሮቻቸው ደብዛቸው ጠፍቶ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራ ጉዳይ፤ አለ? ወይስ የለም?

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ተናግሬ ነበር ማለት ዋጋ የሌለው የወሬ ማጌጫ ነው፤ እስቲ ፍቀዱልኝና ልጠቀምበት፤ ከወያኔ ዋና ምሁር፣ ከመለስ ጋር ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት-ለፊት በቴሌቪዥን በተገኛኘን ጊዜ ‹‹አማራ የሚባል ጎሣ የለም፡›› በማለቴ መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ ብቻ ሳይሆኑ ‹‹አማራ-ነን ባዮች›› በቃልም፣ በጽሑፍም፣ በቴሌፎንም ልክ-ልኬን እየነገሩኝ አንጀታቸውን ቅቤ አጠጥተው ነበር፤ ‹አንዲት ሴት ደውለው እብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል፤› ብለውኛል፤ አንድ ሰው የተናገረው ስሕተት ከሆነ ስሕተቱን በማስረጃ ማጋለጥና የራስን ሀሳብ በማስረጃ መትከል ነው፤ እውቀት የሚዳብረው፣ ሰዎች የሚማሩትና በእድገት ጎዳና የሚጓዙት በተጨባጭ ማስረጃ መነጋገር ሲችሉ ብቻ ነው፤ እኔ አማራ የለም፣ ዜሮ (0) ነው፤ አልሁ፤ አማራ አለ፣ አንድ አለ፤ (1) ነው ያለ ሰው የአንድን ዋጋ ማሳየት አለበት፤ አማራ የለም የሚል ዜሮ ነው ማለቱ ስለሆነ ከሌለ ነገር ምንም አይጠብቅም፤ ከአለ ነገር (ከ1) ብዙ ነገሮችን መጠበቅ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው?

ፐሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤ በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት የደፈጠጡ አገር አልባ ናቸው!

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም (ትርጉም - ነጻነት ገብሬ)

በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ወንጀል ፍፃሜ መሪ ተዋንያን ሆነው ከቆዩ በኋላ በመሰደድ በአሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው በተቀመጡ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ላይ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ መምሪያ ጥቆማእንዲቀርብለት ኢትዮጵያውያንን/ትን በማበረታታት ላይ ይገኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

‹‹… ያኔ በምወደው የጋዜጠኝነት ሙያ እየሰራሁ እቀጥላለሁ››

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ (ከቃሊቲ እስር ቤት)

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ

ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ከታች በፎቶግራፍ የምንታይ [ፎቶግራፉን ያነሳው አብነት ረጋሳን ጨምሮ] ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ“pen Golden of freedom 2014″ ተሻላሚ በመሆኑ ‹‹እንኳን ደስ ያለህ›› ለማለት ኬክ አስጋግረን ወደቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡ቁጥራችን መብዛቱ በቃሊቲ ያሉ ፖሊሶችን ግር ማሰኘቱ አልቀረም ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ