“ጅብ ቲበላህ በልተኸው ተቀደስ”

ከጸጋዬ ገብረመድኅን አርአያ

ወያኔዎች አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነበሩትን ዕለታት ክንውኖች በሥርዓት የመመዝገብ ልምድ ያለው ሰው የሚያሰፍራቸው ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ይኖሩታል። ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ። የእኔን የመጀመሪያ ዕለት አጭር ማስታወሻ ልንገራችሁ። በማለዳ ተነስቼ ጋቢዬን አጣፍቼ ከበሬ ላይ ቆሜ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው አህዮች ወደ መሐል ከተማው (አዲስ አበባ) ሲጓዙ አያለሁ። ያንኑ ያህል ባራባሶ ጫማ የተጫሙ፣ የአካል ዝለት የሚታይባቸውና ከእህል ጋር ከተለያዩ አያል ቀን የሆናቸው የሚመስሉ “ሰብአዊ ፍጥረቶች” አብረዋቸው ይሮጣሉ። ሲያሳዝኑ! ቆይ ቆይ…ከፓስተር ኢንስቲቱት በር ላይ አንድ ጥይት ተተኰሰ። ሌላ ጥይት- ሌላ ጥይት! ሰዎቹ ካለፉ በኋላ ወጣ ብለን ያየነው ሟች በሰፈሩ እንደ ሕሊና ሕመምተኛ የሚታወቅ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እየሳቁ ማልቀስ! (የማለዳ ወግ)

ነቢዩ ሲራክ

በለጋ እድሜዋ ትዳር መስርታ ሁለት ትጉህ መንታ ልጆች የታደለች እህት ከትዳር ጓደኛዋ ችግር ገጠማት። የ “ተበዳይ ነኝ!” ባይ ወዳጀን ምሬት ደጋግሜ ብሰማም ከቀናት በፊት “በደለኝ!” ያለችው የትዳር አጋሯ በኮሚኒቲው ሽምግልና ኮሚቴ በኩል ክስ መስራቱን እና የክስ ጥሪ እንደደረሳት ሰማሁ። ከአሰር አመት በፊት እድሜዋ ገና የ17 አመት እያለ የዛሬ የ12 አመት እድሜ የሆነውን ትልቁን ልጀን ያሳደገችውን እህት የቆየ አብሮነት ትውስታ እያሰብኩ የአለመግባባቱን ሽምግልና ወደሚከወንበት የጅዳ ኮሚኒቲ ሽምግልናውን ለመታዘብ መጓዝ ጀመርኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዘር ማጥራት ወይስ ኢህአዴግን ማፍረስ?

ተመስገን ደሳለኝ Temesegen Desalegnተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ) 

ኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ በርካታ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች … ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን አልዘነጋሁም። እኔም ከ“ፍትህ” ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኛ ነገር፤ የኛ ፖለቲካ፡ ግንቦት ሰባት ምን ነካው?

ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ-ካናዳ) 

እንደመግቢያ፡ ግንቦት ሰባት ምን ነካው?

፩-      ልረብሽ ነው፡፡ ልክ እንደኢሳት ሁሉ፤  "ግንቦት ሰባትም የኛ ነው" ( "የኔ ነው" የሚለው መፈክር አይመቸኝም)፡፡ የኛ ለሆነ ነገር ደግሞ ፍቅራችንን የምንገልጸው፤ በጭብጨባና በሽብሸባ ብቻ ሳይሆን፤ በተግሳጽና በትችትም ጭምር ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ለድርጅታቸው ካላቸው ጽኑእ ፍቅር የተነሳ፤ ድርጅታቸውም መሪዎቻቸውም ሲሳሳቱ፤ መተቸት የሌለባቸው ብጹአን አድርገው ይወስዱኣቸዋል፡፡ በዚህ አልስማማም፡፡ ስለዚህ፤ ግንቦት ሰባትን/የሊቀመንበሩን ቃለምልልስ ትንሽ ልተች ነው፡፡ ይህንን ነው ረብሻ ያልኩት፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምርጫ ሽር ጉድ በ2015ቷ ኢትዮጵያ

Victory Over Tyranny in Ethiopiaፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)

በ2015 በሚካሄደው ፓርላሜንታዊ “ምርጫ” መቅረብና መወሰን ያለበት አንድ ጥያቄ ይህ ነው፤ “የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁን እ.ኤ.አ 2014 ያሉበት የኑሮሁኔታ ከቀድሞ 2010 ወይም 2005 ከነበሩበት የኑሮ ሁኔታ ይሻላል ወይ?” ህዝቦች ካለፉት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ ላይ የማይገኙ ከሆነ አንደ አሮጌ ሸማ መቀየር መቀየር ይኖርባቸዋል። የፖለቲካ ሰዎችና እንደ አሮጌ ሸማ ናቸው። በየጊዜው ካልታጠቡና ካልተለወጡ ይበሰብሳሉ ይገማሉም። በጣም የሚገርም ነገር ነው! ምስኪን ኢትዮጵያውያ አንድ የበሰበሰ የገማ ሸማ ለሌላ 5 ዓመታት በጠቅላላው ለ25 ዓመታት ስትለብስ አያሳዝንም? 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መልካም የእናቶች ቀን

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ(የልጆቻችሁ እስር አንጀታችሁን ላሳሰራችሁ)

ጽዮን ግርማ

እኔና ጓደኛዬ (ሊሊ) የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ)ን ደጅ የረገጥነው በጠዋት ነበር። ምግብ ማቀበል እንጂ ማግኘት ስለማይቻል የግቢው በር እንደተከፈተ ለልብ ወዳጃችን የወሰድነውን ቁርስ ሰጥተን ያደረ ተመላሽ ዕቃ እስኪመጣልን ከመግቢያው ፊት ለፊት ባለው ድንጋይ ላይ ቁጭ ቁጭ ብለናል።ቀዝቀዝ ባለው አየር ላይ ጥቂት ካፊያ ስለነበር ቅዝቃዜው ኩርምት አድርጎናል። ጥቂት ቆይቶ አንዲት እናት በስስ ፌስታል አንድ አራት የሚኾን ፓስቲ (ቤት ውስጥ የሚጠበስ ቂጣ መሰል ብስኩት) ጠቅለል አድርገው ይዘው ወደኛ መጡ ፊታቸውን ጭንቅ ብሎታል። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእስረኛው ‹‹ጋዜጠኝነት›› ሌላ ፈተና

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የ2012ቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳታዊ ምርጫ ከመከናወኑ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ስለምርጫውና የአሜሪካ የጋዜጠኝነት ኹናቴ እንዲወያዩ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አዳራሽ ከተጋበዙና ከሰማንያ የዓለም አገሮች ከተውጣጡ አንድ መቶ ሠላሣ ተሳታፊ ጋዜጠኞች መካከል አንዷ ነበርኹ። ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ከተጋበዙ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጠኞች መካከል ታዋቂው የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ ቦብ ውድዋርድ አንዱ ነበር። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሬየን አልሸጥም

ሄኖክ የሺጥላ
አዲሱን ( የነበረውን ግን ሰሞኑን የሾረውን ) የ " ኦሮሞ ወጣቶች " ግድያ። በነገራችን ላይ ለምንድን ነው " የኢትዮጵያ ወጣቶች " የማንለው ? ማለት ስለማንፈልግ ? ወይስ ብንል ባንል ምን ይጠቅማል ( ምንስ ይጎዳል በሚል ሃሳብ ?) ሁለቱንም ያዙልንና እንቀጥል። ሰሞኑን አምቦ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ወዳጆች " ልጅ ሄኖክ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር በል እንጂ" ጠላቶች ደሞ " አንተ ምንትስ አማራ አሁን አማራ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ መከራ የደረሰበት አምሳ ገጽ ጽፈህ ፣ ነገሩን ለውጠሕና ለጥጠህ ባቀረብከው ነበር '' የሚሉ መልዕክቶችን አስቀምጠውልኛል። እኔም እንደ ለገዳዲ ሬዲዮ " ጦማሪዎችች ሆይ ምልእክታችሁ ደርሶኛል ለሁሉም እንደነገሩ ለመመለስ እንሆ--"

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኃይለማርያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

በ2005 ዓ.ም መጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም “ጠቅላይ ሚኒስትር” ተደርጎ በኢህአዴግ ሲሾም፤ በፓርቲው ውስጥ አክራሪ ብሔርተኛ የአመራር አባላት ከመኖራቸው አኳያ፤ መቼም ቢሆን “ራሱን ችሎ ይቆማል” ብሎ መጠበቁ ተምኔት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ኃይል እንኳን እንደ ኃይለማርያም ላለ የድል አጥቢያ መሪ ቀርቶ፣ ከድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ እስከ ምኒሊክ ቤተ-መንግስትም ድረስ ታላቅ የተጋድሎ ታሪክ ለነበረው አቶ መለስም ቢሆን ክፍተት ካገኘ አለመመለሱን የ93ቱ ሣልሳዊ ህንፍሽፍሽ በግልፅ አሳይቶ ማለፉ አይዘነጋም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ትንሹ” ተስፋዓለም

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Journalist Tesfalem Weledeyes, ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ
ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ

በአነጋገሩ ቀጥተኛና በጠባዕዩ ገራገር ነው። ‹ጥርስ ያሳብራሉ› በሚባሉ ስብሰባዎች፣ በኃይለ ቃል በተሞሉ የኤዲቶሪያል ውይይቶችና ግምገማዎች ሳይቀር ስሜቱን ውጦ በተረጋጋ መንፈስና በለዘብታ ቃል መመላለስ ጸጋው ነው። በኤዲቶሪያል ጠረጴዛዎችና ዴስኮች ዙሪያ በሐሳብ ለመግባባት ከሚደረጉ ግብግቦች ውጭና ባሻገር ቂምና በቀል አያውቅም። በደሙ ውስጥ ከሚዘዋወረውና ራሱን ከሰጠለት የጋዜጠኝነት ሞያውና የጋዜጠኝነት መርሕ የተነሳ ሌላ ዓለም፣ ሌላ ጥቅም፣ ሌላ ኑሮ ያለም አይመስለው። ለእርሱ ኑሮው፣ ለእርሱ ዓለሙ ተጨባጭ መረጃን ከወገናዊነት በጸዳ መልኩ ለሕዝብ ማድረስ ነው - ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ