የአባቶች ስንብት…

ተመስገን ደሳለኝ - አዲስ አበባ

…ከ97ቱ በእጅጉ የተቀዛቀዘው የ2002ቱ ምርጫ የቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል፤ ከመቼውም በላይ የፖለቲካ ምህዳሩን ያጠበበው ገዢው ግንባር፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገውን የምረጡኝ ክርክር እንደ 97ቱ በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍም ሆነ በአዳራሹ ታዳሚዎችና ታዛቢዎች እንዲገኙ አልፈቀደም፤ በዚህ ክርክር ላይ ኢህአዴግ እንደተለመደው ለመጀመሪያ ጊዜ ካቀረባቸው ጥቂት አፈ-ቀላጤዎቹ መካከል የተመልካችን ትኩረት በመሳብ ጎልማሳው የወራቤ ፍሬ ሬድዋን ሁሴንን የሚተካከል አልነበረም፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሰልፍና ሰደፍ፤

ልጅ ተክሌ (ቶሮንቶ)

ዘመቻ ነቀምትና ዘመቻ ኢትዮጵያ

፩-      የሲያትሉ ባተሌ ወዳጄ ደውሎ፤ "አንድነት የአዲስ አበባውን ሰልፍ ፈቃድ ተከልክሏል፡፡ ስለዚህ ምን ርምጃ ይውሰድ" በሚል ጥያቄ ሲያደርቀኝ ነበር፡፡ ሳንግባባ ተለያየን፡፡ ከሞላ ጎደል እሱ የሚለው፤ "ቢከለከሉም ገፍተው ይውጡ፡፡ ምክንያቱም፤ በተከለከሉ ቁጥር እሺ ብለው የሚገቡ ከሆነ፤ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያጣሉ፡፡ ገፍተው ከወጡ ግን፤ መንግስትም ጨክኖ ርምጃ አይወስድም፤ ቢወስድም ግን፤ ትግሉን ያበረታል፤ ሌሎችንን ይቀሰቅሳሉ" ነው፡፡ ኢፍትሀዊ ህግን መጋፈጥ ፍትሀዊነት ነው የሚለውን ይትበሀል ይዞ መሰለኝ የሞገተኝ፡፡ እኔ ደግሞ "የለም ሁሉንም ሰብስቦ ያስራቸዋል፤ ካሰራቸው ደግሞ ሌሎች ሰልፈኞች መውለድ አመታት ይፈጃል፡፡ ስለዚህ ይታገሱ፤ ሲሆን ሲሆን ወደፍርድቤት ይሂዱ፤ ወይም ሌላ ጥበብ ፈጥረው ሂደቱን ያጡዙት፡፡ እንጂ፤ አሁን ገፍተው ሰልፍ ቢወጡ ትግሉን ማጨናገፍ፤ ማስወረድ ነው" ብዬ ሞገትኩ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሚታደስ ቃል ኪዳን

ጸጋዬገ ብረመድኅን አርአያ

“ መኳንንቶቼ፣ ልጆቼና ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ስለ እናቴ ኢትዮጵያ ሕይወቴን ልሰዋላት ሙሉ ፈቃድ አለኝ። በእኔ ልብ ያለው አሳብ በትክክል በእናንተም ልብ በመታሰቡ በጣም ደስ ብሎኛል። “ እንግዲህ አሳባችን አንድ ከሆነ ጠንክሩ እንጂ አትፍሩ። ለዘመቻውም አዋጅ አናግራለሁና አይዞአችሁ አትፍሩ! “ አገሬ ሆይ ስሚ! መኳንንቶቼ፣ ወታደሮቼ፣ ሕዝቦቼ ስሙ…..ወደፊት ገስግሱ እንጂ ወደኋላ አትቅሩ! “ የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ! ልብ አድርገህ ተመልከት ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት! ሁለተኛ ዘውድህ ናት! ሦስተኛ ሚስትህ ናት! አራተኛ ልጅህ ናት! አምስተኛ መቃብርህ ናት! እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀኸው ተነሳ!”

አንበሳው አጼ ዮሐንስ- ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! (ክፍል ሶስት)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ከአዲስ አበባ)

ልዕለ ኃያሏ ሀገረ-አሜሪካን ዛሬ ለተጎናፀፈችው የሕግ የበላይነት የተከበረበት ሥርዓት መሰረት የጣሉት እነ ቶማስ ጃፈርሰን በነፃነት አዋጃቸው ላይ ‹‹ሁሉም ሰዎች በእኩልነት የተፈጠሩ ናቸው›› በማለት ሲደነግጉ፤ እንግሊዛዊው ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል ደግሞ “Animal Farm” በሚለው መፅሐፉ፣ ጉልበታም ‹‹ገዥ›› አድርጎ በሳላቸው ገፀ-ባሕሪያት አማካኝነት ‹‹…አንዳንድ እንስሳት (ሰዎች) ግን የበለጠ እኩል ናቸው›› ይለናል። በርግጥ ሁለቱም አይነት አስተዳደሮች መሬት ወርደው ዓለማችንን ዲሞክራት እና አምባ-ገነን በማለት በሁለት ጎራ የከፈሉ የመሆናቸው ጉዳይ አከራካሪ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሁለት ባሪያ ነጻ የሚወጣው መቸ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቅድለት

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

አንድ በሀርቫርድ የኒቨርሲቲ ያጋጠመኝን ነገር መግቢያ ላድርገውና ልቀጥል፤ በአንድ ሴሚናር (የጥናት ውይይት) ላይ አንድ ጥቁር አሜሪካን ፕሮፌሰር ወደአሜሪካ በባርነት በመጡት አፍሪካውያን ላይ የተፈጸመውን ግፍ በመዘርዘር አስረድቶ አሁን ለእነሱ ልጆችና የልጅ ልጆች ካሣ መከፈል አለበት የሚል ክርክር አነሣ፤ ካሣውን የመክፈል ግዴታ የሚጣለው ማን ላይ ነው? ካሣውንስ የመቀበል መብት የሚሰጠው ለማን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ሳናነሣ ብዙ ሌሎች ጥያቄዎች ይኖራሉ፤

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴሌፎኑ 'ለግዜው' ጥሪ አይቀበልም

Ethio-telecom sucks!ክንፉ አሰፋ

"የደወሉላቸው ደንበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም። ..." የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልዕክት ያላጋጠመው ቢኖር ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የስቅለቱ እና የትንሣኤው አብነት

ስቅለትከሆሳዕና እስከ ማዕዶት

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል ተከብሮ የሚውለው፣ በዕለተ እሑድ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በዕለተ እሑድ-መጋቢት 29 ቀን ነው። የግዕዝ ቋንቋ ሊቃውንት እንደሚተረጉሙት ከሆነ፣ “ትንሣኤ ማለት-መነሳት ማለት ነው።” ሞትን ድል አድርጎ፣ ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው። “ሕይወት ማግኘት፣ ነፍስ መዝራት፣ ሕልው መሆን” ማለት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ረዥም ጥቁር ጥላውን በ(መካከለኛው) አፍሪካ ጥሎአል

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

የ1994 የሩዋንዳ የጭፍጨፋ እና የእልቂት ጸጸት በ2014 የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰማይ ላይ እያንዣበበ ነው!

ባለፈው ሳምንት የሩዋንዳ ህዝብ እርስ በእርስ የተራረደበትን 20ኛውን ዓመት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት መጥፎ ገጽታ ለማስታወስ የሀዘን ሳምንት አውጆ ድርጊቱን በመራር ሀዘን ዘክሮታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሰማያዊ ፓርቲ የሚታገለው ማንን ነው?

ግርማ ካሳ

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ አነበብኩ። ገረመኝ። መጋቢት 28 ቀን በአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጉን ባፈረሰ መልኩ በመጋቢት 28 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እስክንድር ነጋ እስርና ወከባ (ጫና)

በግርማ አንድሪያስ  (ኔዘርላንድ፡ ኣምስተርዳም)

''... ጋዜጠኞችና ኣስታሚዎች በጥብቅ መታሰርና በገንዘብ መቀጣት የጀመሩት የፕሬስ ኣዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ከሶስት ወር በኋላ  ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የካቲት 1984 በአትዮጵያ ኣቆጣጠር። ታስረው በፕሬስ ህጉ የተከሰሱና ለመጀመሪያ ጊዜ በፍርድ ቤት ተከራክረው ነጻ የወጡት፣ በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደረው የአዲስ ዘመን ጋዘጣ ኣዘጋጆች ናቸው። ኣዘጋጆቹ የታሰሩትና የተከሰሱት በጋዜጣው ላይ በ ኢትዮጵያ የዲሞክራሲን ጎጂና ጠቃሚ ገጽታዎች የሚዳስስ  ጽሑፍ በማውጣታቸው ነው።''

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ