ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ - መልክአ ኢትዮጵያ - ፮

ጽዮን ግርማ Tsion Girmaጽዮን ግርማ
ምስክርን የማውቀው ኢትዮጵያ ነው፤ ዛሬ አገኘኹት። በእናቱ ጫንቃ ላይ የነበረው ያ ሁሉ አይበገሬነት ጠፍቶ በፋርመርስ ሥጋ ቤት አንገቱን ደፍቶ ሥጋ ቆራጭ ኾኗል። ምስክር የወጣበት የውስጠኛው ክፍል የገባው ሥጋ ተስተካክሎ እየተቆራረጠ ለገበያ የሚዘጋጅበትና የሥጋ ዘሮቹን ተከትለው የሚመጡትን ቆሻሻዎች ማጽዳት ነው። ምስክር በቆምንበት የተሻለ ኑሮ እየመራ ስለመኾኑ አጠር አጠር አድርጎ ነገረኝ፤ ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሰሜን ኮሪያና ወጣቱ ዝንጀሮ

ይነጋል በላቸው

ከተቀረው የእንስሳት ዓለም በአእምሮ የብስለት ደረጃ (አይ ኪው) ወደሰው ከሚጠጉ ሌሎች እንስሳት ውስጥ ዝንጀሮ አንደኛው ነው። አንዱን የዝንጀሮ ታሪክ ቀጥለን እንይና ከሰሜን ኮሪያ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር እናመሳስል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ሮ አዜብ ስለየትኛው ድህነታቸው ነው ሊነግሩን የፈለጉት?!

ወ/ሮ አዜብ መስፍን W/z Azeb Mesfinፍቅር ለይኩን

በ2000 ዓ.ም. ይሁን በ2001 ለጊዜው እርግጠኛ ባልሆንም ግን ከሁለቱ በአንዱ ዓመት ይመስለኛል። በመዲናችን በአዲስ አበባ ላይ በተካሄደ ዓመታዊው የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ የአፍሪካ ቀዳማይ እመቤቶችም በበኩላቸው ከባሎቻቸው እኩል አፍሪካውያን እመቤቶች ስለ አፍሪካ ጉዳይ ተፈጥሮ የተቸራቸውን የሴትነት ጥበብና ብልሃታቸውን በመጠቀም ኁልቆ መሣፍርት ለሌለው ለአፍሪካና ለአፍሪካውያን ችግሮችና እንቆቅልሾች ምክር ቢጤ ለመለገስና መፍትሔ ለማመላከት እነርሱም በተራቸው ለስብሰባ ተቀምጠው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አፈወርቆች

ዶ/ር ከበደ ሚካኤል Dr. Kebede Michaelኤፍሬም እሸቴ

ከሰሞኑ "ፋኖስና ብርጭቆ" የምትባለውን የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤልን ግጥም በፌስቡክ ገጼ ላይ ለጥፌ ነበር። "ስንቶቻችሁ ይህንን የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤልን ግጥም ታስታውሣላችሁ? በልጅነቱ ይህንን በቃሉ ይወጣ የነበረ አሁንም ያልረሣ ካለ እነሆ ካንገቴ ዝቅ ብዬ አክብሮቴን ልግለጽ" ከሚል ማስታወሻ ጋር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትግል ... ሽንፈት፤ ... ድል፤ ሽንፈት ...

ተመስገን ደሳለኝ

ከምሽቱ አንድ ሰአት አልፏል፤ የእጅ ስልኬ ደጋግሞ ቢጮኽም ትኩረት አልሰጠሁትም። ከጥቂት ሰከንዶች ፋታ በኋላ የቢሮዬ ስልክ ጮኸ፤ አነሳሁት። ለካስ እንዲህ በአንዱ አልመልስ ስላት፣ በሌላው እያፈራረቀች የምትደውለው ዕድሜዋ ወደ ሰባ እየተጠጋ ያለው አሮጊቷ እናቴ ኖራለች፦

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዳምጠው ወያኔ/ኢሕአዴግና አፈና በኢትዮጵያ

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በቀልድ ልጀምር፤ አንድ ጮሌ የአስመራ ልጅ የእኔ ተማሪ ነበር፤ አንድ ጊዜ የጂኦግራፊ ክፍል ተማሪዎች አንድ ጃፓናዊ አስተማሪ ለመሸኘት ግብዣ አድርገው ነበር፤ በግብዣው ላይ የጠቀስሁት ነገረኛ የአስመራ ልጅ (የአስመራ ልጅ የምለው ላርቀው ፈልጌ እንዳይመስላችሁ፤) በአስተማሪዎች ላይ ቀልድ ያሰማ ነበረ፤ ስለኔ ሲናገር፤– መስፍን ወልደ ማርያም የቢሮውን በር ሁልጊዜ ክፍት አድርጎ የሚቀመጠው ለምንድን ነው? ይልና እሱው ሲመልስ፣

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ድሀ ከሆኑ አይቀርስ - ልክ እንደ አቶ መለስ

ወ/ሮ አዜብ መስፍንኤፍሬም እሸቴ

ሰሞኑን በተካሔደው የኢሕአዴግ ጉባዔ ላይ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ያደረጉትና በኢቲቪ የዜና ዕወጃ ላይ የቀረበው ንግግራቸው የማኅበራዊ ድረ ገጾች የመወያያም የመሳሳቂያም የመሳለቂያም ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ነበር። "#SomeoneTellAzebMesfin" በሚል "ሐሽ ታግ/ #Hashtag" (ቅምር-ቃል ልበለው?) በትዊተር ላይ ኢትዮጵያውያን የግል ሐሳባቸውን ሲሰጡበት የቆዩት የወይዘሮዋ ንግግር ያተኮረው በአቶ መለስ ደሞዝና ድህነት ላይ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዞምቢዎቹ እየመጡ ነው!

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

ሐምሌ 11 ቀን ዓ.ም. በታተመችው በ"አዲስ ነገር" ጋዜጣ ወዳጄ መስፍን ነጋሽ "ዞምቢዎቹ" በሚል ርዕስ ዛሬም ድረስ ከህሊናዬ ያልጠፋ ድንቅ ጽሁፍ አስነብቦን ነበር (የዚህ ፅሁፍ ሃሳብም ከዚሁ የተናጠቀ ነው)። ይኸ ከሆነ ድፍን ሶስት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ብቻ ቀርቶታል። "አዲስ ነገር" ም ወደ ታሪክነት ከተቀየረች ሁለት ዓመት አልፏታል። ለምን? ... ዞምቢዎቹ ድል ስለነሷት፤ እንዴት? ማንም ዞምቢዎቹን ድል አድርጎ ስለማያውቅ። ዞምቢ ምንድር ነው? ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ እንዲህ ገልጿቸዋል፦

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነገን የተሻለ ቀን ለማድረግ፤ ዛሬ ነው መነሳት፤

ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)

ይድረስ ለሀገሬ ወጣቶች
ከዘር ማንነታችን በፊት ሰብአዊ ሰውነታችን፤ ከጎጠኝነታችን በፊት ኢትዮጵያዊነታችን፤ ከሸፍጥ፤ ከተንኮል፤ ከመሰሪነታንችን በፊት ቅንነታችን፤ ከፍርሀታችን በፊት ድፍረታችን፤ እርስ በርስ ከመጠራጠራችን በፊት መተማመናችን፤ ከመፍረክረካችን በፊት በጽናት መቆማችን፤ ከልዩነታችን በፊት አንድነታችን፤ ወያኔ ዛሬ ኢትዮጵያውያንን ከከተተበት መቀመቅ ውስጥ የሚያወጣን ብቸኛ መፍትሄ ከላይ የደረደርኩት ነገር ብቻ ይመስለኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ