የፒያሣ ልጅ ከፍቅሩ ኪዳኔ Yepiassa Lij by Fikru Kidaneደራሲ - ፍቅሩ ኪዳኔ

ቅኝት - መስፍን ማሞ ተሰማ

መነሻ

በምኖርበት ከተማ ሲድኒ ውስጥ የአማርኛ መፃህፍት አስመጪና አከፋፋይ የለም። ይህንን ችግር የሚያውቁ በሜልበርን ከተማ የሚኖሩ ወዳጆቼ ባመቻቸው ቁጥር የኢትዮጵያዊያን መናኸሪያ ወደ ሆነችው ‘ፉት ስክሬይ’ ወደምትባለው ቀበሌ እየዘለቁ በዚያ ከሚገኝ የመፃህፍት መደብር የአውስትራሊያን ምድር ከረገጡት አዳዲስ የአማርኛ መፃህፍት መካከል የቻሉትን ያህል ይልኩልኛል።

 

ከእለት የህይወት ኑሮ ሩጫ ባሻገር ከሚቀረው ጊዜ አንፃር በእጄ ገብተው ለመነበብ ‘ወረፋ’ ሲጠብቁ ከሰነበቱት መኻል ‘የፒያሳ ልጅ’ን አነበብኩ። እና እንደደረሰኝ ማንበብ ባለመቻሌ የህሊና ቁንጥጫ ተሰማኝ። ለምን? ምክንያቱም ይህንን መፅሀፍ ማንበብ የሚችል ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያነበው ዘንዳ የሚገባ ነው ብዬ በማመኔ። ደግሞም ይህንን እምነቴን ቀደም ብዬ ለአንባብያን ማካፈል ባለመቻሌ። በ’ፒያሳ ልጅ’ ላይ ላካፍላችሁ የምፈልገው ምንድን ነው? ለምላሹ እነሆ ‘የፒያሳ ልጅ’ … (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ