Animal farm የእንስሳት አብዮትበአቢይ አፈወርቅ

ጆርጅ ኦርዌል ናፖሊዮን የተባለውን መሪ ባህሪ ሲቀርፅ፤ “መለስ ዜናዊ የሚባል አምባገነን ይነሳል” በሚል ትንቢት አልነበረም። ይሁንና የአሁኑ የኢትዮጵያ መሪ ከኦርዌሉ ናፖሊዮን ጋር እጅግ የተማሰለ ባህሪ ይዞ ስናይ በርግጥ ይህ መፅሀፍ ስለዛሬይቱ ኢትዮጵያ የተፃፈ ያህል ነው የሚሰማን።

 

ናፖሊዮንና ስኖውቦል ራሳቸውን በነፃ አውጪ ስም ለንግስና ያጩ የስልጣን ጥመኞች ነበሩ። ስኖውቦል በመጠኑ ሻል ያለ አእምሮና ህልም ሲኖረው ናፖሊዮን ደግሞ አእምሮው ለሴራ የተሳለና ተቀናቃኙን ውሎ አድሮ ለመጣል ቀድሞ የሚዘጋጅ ፈጣን ጉልበታም ነው። የነዚህ ተቀናቃኞች ፍልሚያና ውጤቱን ስናነብ አቶ መለስ በትግሉም ወቅት ሆነ ከቤተ መንግስት ሆነው የስልጣን ተጫራች ተጋዳላይ ጓዶቻቸውን እንዴት ጠልፈው እንደጣሏቸው ነው የሚታሰበን። አቶ አረጋዊን በበረሃ፤ አቶ ስዬን በአዲስ አበባ ያስታውሷል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ