ለሀይማኖት መሪዎችና ለኢትዮጵያ ማህበረሰብ አመራሮች (አኢጋን)

በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን እየተካሄደ ባለው ጭቆና፣ ግድያ፣ አፈና፣ እስራት፣ ስራ እጥነት፣ ወዘተ ምክንያት ከሀገራችን እኮበለሉ ወደተገኘው ቦታ ጥገኝነት ለማግኘት የሚሞክሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱ በቅርብ ጊዜ የተከሰቱት ሁኔታዎች ግልጽ አመልካቾች ናቸው። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

ለሕጋዊው ሲኖዶስ የተጻፈ ግልጽ ደብዳቤ

ከፖርትላንድ ኦሬገን ቅድስት ማርያም ምዕመናን

ከሁሉም በፊት የእግዚአብሔር ሠላምታችን እናስቀድማለን። ይህን ግልጽ ደብዳቤ እንድንጽፍ ያነሳሳን ወይም ያስገደደን በአጥቢያ ቤተክርስትያናችን ማለትም በፖርትላንድ ኦሬገን የደብረ-ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን አገልጋይ ካህን በሆኑት ቀሲስ ኤፍሬም የኋላሸት እና በምእመናን መካከል ያለው ሥር የሰደደ ችግር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአትላንታ ነዋሪዎች በወ/ት ብርቱካን የክብር እንግድነት ውዝግብ ላይ መግለጫ አወጡ

በአትላንታና አካባቢዋ የሚገኙ የሲቪክ ማህበራት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የከተማዋ ነዋሪዎች የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የክብር እንግድነት መሰረዝ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽና ጥቂት ያሏቸው የቀድሞ የፌዴሬሽኑ አመራር አባላት የተሻረው ውሳኔ እጅግ ያሳዘናቸው መሆኑን ባወጡት መግለጫ አስታወቁ። በሚቀጥለው አመት 2011 የሚካሄደው የሰሜን አሜሪካ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል በአትላንታ እንደሚካሄድ ይታወቃል። (የመግለጫውን ሙሉ ቃል ይህንን በመጫን ያንብቡ!)

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በእንግሊዝ

“የንቅናቄያችን የእንግሊዝ አገር ስብሰባ ስኬታማ ውጤቶች” ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ

ባለፈው ሳምንት መጠናቀቂያ አካባቢ በእንግሊዝ አገር ሪዲንግ ከተማ በአገራችን ስላለው ”የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የመሬት ነጠቃ እና የፖለቲካ መብቶች ረገጣ” የንቅናቄያችን የእንግሊዝ ንዑስ (chapter) የሁለት ቀን ስብሰባ አካሂዶ ነበር። በተለይ በስብሰባው መጠናቀቂያ ላይ ከዚህ በፊት ጎራ ለይተው እርስበርስ በዘር፣ በዓላማ፣ በአካሄድ፣ በፕሮግራም ወዘተ የነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ቡድኖች - የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሲዳማ ተወላጆች እንዲሁም ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ክርስቲያኖች፣ እስላሞች፣ የአንድነት ደጋፊዎች፣ የነጻ አውጪ ግንባሮች፣ የትጥቅ ትግል ደጋፊዎች፣ የሰላማዊ ትግል አራማጆች፣ ወዘተ - በአንድ ቦታ ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በስብሰባው መጠናቀቂያ ወቅት ሲተቃቀፉ፣ እርስ በርስ በፈገግታ ሲነጋገሩ እንዲሁም የግል መረጃዎቻቸውን ሲለዋወጡ መመልከቱ ብቻ የስብሰባውን ስኬት በግልጽ የሚያሳይ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፈጣን ምላሽ የሚጠይቅ የኅብረት ጥሪ

የህወሓት/ኢህኣዴግ መንግሥት ሥልጣን ከጨበጠበት ከ፩ሺ፱፻፰፫ ዓ. ም. (1991 አ.አ.) ጀምሮ የኢትዮጵያን ሀገራዊ ሉዓላዊነት እየሸረሸረና የሕዝቡን መብት እየረገጠ ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት ሆኖ መውጣቱ ዛሬ ከምንም ጊዜ የበለጠ ግልጽ ሆኗል። ያለፉት 19 ዓመታት የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ኢትዮጵያ ድንበርዋ እንዲደፈር፤ ህዝቧ በዘር እንዲለያይና እርስበርስ እንዲጣላ፤ የኢትዮጵያ መሬት በርካሽ ዋጋ ለውጭ ባለህብቶች ተሸንሽኖ እንዲሸጥ በአንጻሩ ደግሞ በርሃብ የሚጠቃው የሚሰቃየውና የሚሞተው ሕዝብ ቁጥሩ እንዲያሻቅብ የሆነበት፤ ብልጭ ብሎ የነበረው የዴምክራሲ ጭላንጭል የጠፋበት፣ ፍትኅ ጠፍቶ ዜጎች ሲዋከቡ ሲታሰሩ ሲደበደቡ ሲገደሉ ሲሰደዱ ዘወትር የምናይበት፤ የሀገሪቱ ሃብት በጥቂቶች፣ በሥልጣን ኮርቻ ላይ በጉልበት በወጡ አምባገነኖች እየተዘረፈ መሆኑን በየዕለቱ የምናይበት ዘመን ነው። (… ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)