ድጋፍ አሰባሳቢዎቹ መልስ አላቸው

በኢ/ር ኃይሉ ሻውል የሚመራው ቡድን ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን እና እሁድ ሰኔ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔ አድርጎ አመራሮቹን መምረጡ አይዘነጋም። በጠቅላላው ጉባዔ ም/ፕሬዝዳንትና የሰሜን ኢትዮጵያ ቀጠና ኃላፊ ሆነው የተመረጡት አቶ አባይነህ ብርሃኑ፤ የጉባዔው መዝጊያ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

 

በዕለቱ የቀድሞው የቅንጅት አመራሮች ከእስር ከመፈታታቸውም ሆነ ከተፈቱ በኋላ በውጭ አገር የሚገኙ ቻፕተሮች ያሰባሰቡት ገንዘብ በቅንጅት ስም በመሆኑ ሊመልሱላቸው እንደሚገባ አቶ አባይነህ አምርረው ተናግረዋል። ይህ ካልሆነ ግን ጉዳዩን ወደ ሕግ በመውሰድ ገንዘቡን ገቢ እንደሚያደርጉም ዝተው እንደነበር መዘገባችን አይዘነጋም።

 

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ከቅንጅት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ አሰባሳቢ ማኅበር ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ አክሎግ ልመንህን፣ በካናዳ የቻፕተሮቹ አስተባባሪ አቶ ዮሱፍ ዑመርን፣ እንዲሁም ከአውሮፓ የስዊድኑን ሊቀመንበር አቶ ታምራት አዳሙን እንቢልታ ጋዜጣ በቅጽ 1፣ ቁጥር 27 ዕትሙ ስለጉዳዩ አነጋግሯቸዋል። ሙሉውን ዘገባ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ