እኛ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ውስጥ የምንገኝ በቅድሚያ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሣት) መቋቋምን አስመልክቶ የተወሰደውን እርምጃ ከልብ የምናደንቅ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን። ይህ ታላቅ ራዕይ ተግባራዊ እንዲሆን ያደረጉትን የአማካሪዎች ቦርዱን፣ የፕሮግራም አዘጋጆችን፣ አርታኢዎችን እና በአጠቃላይ በኢሣት ሥራ ላይ ላለፉት ቀናትና ሣምንታት እንዲሁም ወራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ይህ የቴሊቪዥን ጣቢያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ”ምርጫ” ከመደረጉ በፊት ተግባራዊ እንዲሆን ላደረጉት አስተዋጽዖና መስዋዕትነት ያለንን ታላቅ ምስጋና በከፍተኛ ወገናዊ ኩራት ለመግለጽ እንወዳለን።

 

የተከናወነው ይህ ክቡር ተግባር ለዘመናት በመረጃ እጥረት ሲሰቃይ ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ገፀበረከት ነው። ለነፃነታችን በምናደርገው ትግል እያንዳንዳችን ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የምናበረክተው አስተዋጽዖ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአሁኑ ወሳኝ ወቅት የኢሣት አገልግሎት መጀመር የነፃነት ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ የማሳደግ ታላቅ የሆነ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እንዳለው እሙን ነው። ... (ሙሉውን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ ...)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ