7 Ethiopians killed in tanzaniaኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ታህሳስ ፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 13, 2016)፦ የሰባት ኢትዮጵያውያን አስከሬን በታንዛኒያ ወንዝ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱን የአገሪቱ መንሥግት አስታወቀ። ኢትዮጵያውያኑ ወንዝ ውስጥ ሆን ተብለው የተጨመሩ መሆኑንም ፖሊስ ተናግሯል። አስከሬኖቹ በጆኒያ ከአሸዋ ጋር ተደርገው ነው ወደ ወንዝ የተወረወሩት ሲል ፖሊስ መግለጡን የኬንያ ቴሌቭዥኖች የዘገቡ ሲሆን፣ ሟቾቹ በሙሉ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል።

ይሁንና በዚህ ጉዳይ ላይ በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ዝምታን የመረጡ ሲሆን፣ የታንዛኒያ መንግሥት አስከሬኖቹን ወደ ኢትዮጵያ ይላክ ወይም እዚያው የቀብር ሥነሥርዓት ይፈጽምላቸው እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም።

ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች በሥራ ማጣት ሳቢያ አገር ጥለው ወደ ደቡብ አፍሪካ በታንዛኒያ እያቋረጡ እንደሚሄዱ የሚታወቅ ሲሆን፣ በዚህ በቢልየን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያጋብሱት የህወሓት ደጋፊዎችና አባላቱ እንደሆኑ ይታወቃል።

በተለይም ከደቡብ ኢትዮጵያ በደላሎች አማካኝነት ወደ ኬኒያ፣ ቀጥሎም ወደ ታንዛኒያ የሚሸጋገሩት ኢትዮጵያውያን በአብዛኛው መቀመጫቸውን ኬንያ ያደረጉና፤ በልዩ ስማቸው "አስጨዳጅ" ተብለው የሚታወቁ የህወሓት አባላት ናቸው።

ከአንድ ዓመት በፊት ይህን መሰል ክስ የተደጋገመበት የኢትዮጵያ መንግሥት፤ ለረዥም ዓመታት በኬንያ ይህንኑ ሥራ ከኤምባሲ ሠራተኞች ጋር እጅና ጓንት በመሆን ስትሠራ የኖረች ኢትዮጵያዊት በፖሊስ ታድና ወደ ሀገር ቤት እንድትገባ የተድረገ መሆኑን መንግሥት ቢገልጥም፤ እስካሁን ፍርድ ቤት ቀርባ ምን እንደፈረደባት የታወቀ ነገር የለም።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ