Ethiopian Ministry of Peace

የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር

ስለሰላም መሥራትና በሕዝባችን መካከል መተማመን እንዲኖር መጣር ተገቢ ነው

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 4, 2019)፦ የሰላም ሚኒስቴር ሰሞኑን በተከሰቱ ግጭቶች ተሳታፊ ኾነዋል የተባሉ ተጥርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር እያዋሉ ስለመኾናቸው ገለጸ።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር የማዋሉ ሥራ እየተሠራ ያለው በየደረጃው ካሉ የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር እንደኾነ ገልጿል።

መግለጫው ምን ያህል ተጥርጣሪዎች እንደተያዙ ሳይጠቁም አልፏል። በተያያዘም በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖች መንግሥት እርዳታ እያቀረበ መኾኑን ገልጿል።

ስለሰላም መሥራትና በሕዝቦች መካከል መተማመን እንዲኖር መጣር ተገቢ መኾኑን፣ እንዲሁም ያሉትን የሐሳብ ልዩነቶች ወይም አለመግባባቶች በጠረጴዛ ዙሪያና በሕግ ማዕቀፍ ሥር የመፍታት አስፈላጊነት ላይ በማስመር፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለሰላም ትኩረት እንዲሰጡና “የእኔ ጉዳይ ነው” በማለት በአገሪቱ ሰላም መስፈን ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሰላም ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ጥሪ አስተላፏል።

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ (ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም.) አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ “ተከብቤአለሁ” በማለት በፌስቡክ ያሠራጨውን መልእክት ተከትሎ፤ ለሁለት ቀናት (በአንዳንድ አካባቢዎች ለሦስት ቀናት) ኹከትና ግጭቶች በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች፣ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋና ሐረር ተከስቶ ከ 86 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ