Cocaine at bole airport

ቦሌ ላይ የተያዘው ከ109 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው 47.7 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ኮኬይን

ከ109 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ አለው

ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 16, 2019)፦ ከሁለት ሳምንት በፊት የስናይፐር መለዋወጫዎች የተያዙበት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ዛሬ ደግሞ 47.7 ኪሎ ግራም ኮኬይን አደገኛ አደንዛዥ እፅ ተያዘ።

የገቢዎች ሚኒስቴር እንደገለጸው በቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ተርሚናል ውስጥ የተያዘው ኮኬይን ከ109 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ሲሆን፤ ይህንን አደገኛ እፅ ይዘው የተገኙት አምስት ብራዚላውያን ናቸው።

በጉምሩክ የኢንተሊጀንስና ኮንትሮባንድ ክትትል መሪነት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች ጋር በመኾን በተሠራ ኦፕሬስን ትናንት ኅዳር 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ይኽንኑ 47.7 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ሥር ማዋል ችለዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ