The Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)

ታላቁ ህዳሴ ግድብ

ውይይቱ ላይ የተለያዩ አካላት ተሳትፈዋል

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 17, 2020)፦ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ውይይት እየተደረጉ እንደሚገኙ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል።

በውይይቱ ላይ ሚኒስትሮች ኢትዮጵያን በመወከል በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ድርድር ሲያደርጉ የነበሩት የኮሚቴ አባላት፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ ተሳታፊዎችም የዛሬው የውይይት አካል ናቸው።

ውይይቱ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች አካሔድና አቅጣጫዎች ላይ እንደኾነም ተጠቅሷል።

በኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል በዋሽንተን ዲሲ በህዳሴ ግድቡና በውኃ አጠቃቀሙ ላይ ባለፈው ሳምንት ለሁለት ቀናት ሲመክሩ ቢሰነብቱም ድርድሩ ያለውጤት መበተኑ አይዘነጋም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ