በአየር ፀባይ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌና ላሊበላ የሚያደርገውን በረራዎች ሰረዘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ውስጥ የበረራ መስመሮች
የጎንደር፣ ሽሬና የአክሱም በረራዎቹም ተስተጓጉለዋል
ኢዛ (እሁድ መጋቢት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 15, 2020)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች በገጠመው የአየር ፀባይ ምክንያት፤ ዛሬ ወደ መቀሌና ላሊበላ የሚያደርጋቸውን በረራዎች መሰረዙን አስታወቀ።
ከእነዚህ ሁለት በረራዎች ሌላ ወደ ጎንደር፣ ሽሬና አክሱም ይደረጉ የነበሩ በረራዎችንም መስተጉጎላቸውን ዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2012 ዓ.ም. ጠዋት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የአየር ጠባዩ ስለመሻሻሉ መረጃ እንደደረሰው በረራዎችን የሚቀጥል መኾኑንም አስታውቋል። (ኢዛ)