በኮሮና ቫይረስ ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ሕይወታቸው አለፈ
የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር
ሁለቱም በዛሬ ዕለት ነው ሕይወታቸውን ያጡት
ኢዛ (እሁድ መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 5, 2020)፦ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው በለይቶ ማቆያ ሕክምና እየተደረገላቸው ከነበሩ ታማሚዎች መካከል ሁለተኛው ሰው ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተጠቃ የመጀመሪያው ሰው መሞቱ የተገለጸው በዛሬው ዕለት ሲሆን፣ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ዛሬ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈው ሁለተኛው ሰው የ56 ዓመት ጎልማሳ ናቸው።
የአዲስ አበባ ነዋሪ የኾኑት እኝህ ታማሚ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተረጋግጦ በለይቶ ማከሚያ ሕክምና ሲደረግላቸው የቆየ ቢሆንም፤ ከገቡበት ዕለት ጀምሮ በጽኑ ታመው እንደነበር ተጠቅሷል።
ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ.ም. 12፡00 ሰዓት ላይ ሕይወታቸው ያለፈው እኚን ጎልማሳ ጨምሮ የመጀመሪያው የሞት ሪፖርት በተደረገበት በዛሬው ዕለት ሁለት ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸውን እንዳጡ አመላክቷል። (ኢዛ)



