Axum

አክሱም

ኢዛ (ማክሰኞ ሚያዝያ ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 21, 2020)፦ በትግራይ ክልል በአክሱም ከተማ በለይቶ ማቆያ ማዕከል ውስጥ ገብቶ የነበረ አንድ ግለሰብ፤ ከለይቶ ማቆያው ሊያመልጥ ሲል መያዙንና የስድስት ወር እስራት እንደተፈረደበት ተገለጸ።

ግለሰቡ ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም የተጓዘና ከለይቶ ማቆያው ለማምለጥ የሞከረውና የተያዘው በአምስተኛ ቀኑ ሲሆን፤ ዛሬ በአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት ቀርቦ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ድንጋጌ በመተላለፉ ስድስት ወር እስራት ተፈርዶበታል ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ