አክሱምላይት - ፕሮግራሚንግ በአማርኛና በግዕዝ ፊደላት
በዓለም ላይ ያሉ የቴክኖሎጂ ዕድገትን ካፋጠኑ ግኝቶች አንዱ የኮምፒዩተር ፕሮግራም ነው። በአሁኑ ወቅት የኮምፒዩተር ፕሮግራምን የማይጠቀም ተቋም የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም።
በሃገራችን የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ ከገባ ዓመታት ቢቆጠሩም፤ በዘርፉ የሚፈለገውን ያህል ርቀት ተጉዘናል ማለት ግን አያስደፍርም። ለዚሀም የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ቅሉ፣ በራሳችን ቋንቋ ሶፍትዌር ያለመሰራቱ አንዱ ችግር ነው። የኮምፒዩተር ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና መሰል መተግበሪያ ሶፍትዌር በሙሉ የተገነቡት በተለየ ቋንቋ ሰለሆነ ለሃገራችን ተጠቃሚዎች አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል።
በቅርቡ ግን የኮምፒዩተር ፕሮግራሞችን በአማርኛ ቋንቋ በግዕዝ ፊደል መፃፍ የሚያስችል አክሱምላይት የተባለ አዲስ የነፃ ሶፍትዌር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተገንብቷል። ዝርዝሩን በዚህ ድረገፅ ( http://www.meliyu.com ) መመልከት ይቻላል።
አክሱምላይት ፕሮግራም ምንድነው?
እክሱምላይት በግዕዝ ፊደልና በአማርኛ ቋንቋ ፕሮግራም ለመፃፍ የሚያስችል ኮምፓይለር እና ማቀናበሪያ (Compiler and Integrated Development Environment)ነው። ይህ ሶፍትዌር Windows XP, Windows Vista, Windows 7, Windows Server 2003, Windows Server 2008 ላይ ያለ ምንም ችግር መጫንና መጠቀም ይቻላል። የአክሱምላይት ኮምፓይለር የተወጠነው በአማርኛ ቢሆንም የወደፊት እትሞቹ ኦሮምኛ እና ትግርኛን ያካትታል።
የአሱምላይት ቁልፍ ቃላቶች (keywords)
አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በቀላሉ የሚረዳቸው ናቸው። አክሱምላይት የተከተለው የፕሮግራም ውቅረት (Syntax and Semantics) የዘመናዊ የኮምፒዩተር ቋንቋዎችን (High level programming languages) ስለሆነ በአክሱምላይት የተሰሩ ፕሮግራሞችን አክሱምላይት ኮድ መቀየሪያን በመጠቀም ወደሌሎች ፕሮግራሞች (C# and VB.NET) በቀላሉ መቀየር ይቻላል።
የአክሱምላይት አርታኢ (Code Editor)
የራሱ የሆነ ቁልፍ መምቻ መድበል (component) ስላለው ተጨማሪ የቁልፍ መምቻ ሶፍትዌር (Keyboard mapper) አያስፈልገውም። ይህ መድበል አማርኛ እና እንግሊዝኛ ሆሄያትን በቀላሉ ለመፃፍ ያስችላል።
ስለ አክሱምላይት ያለዎትን አስተያየት ለሶፍትዌሩ መሓንዲስ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ በቀጥታ መላክ ይችላሉ።
Meshesha Kibret Cherie
Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.