Total coronavirus cases in Ethiopia, 2020-05-01

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ (ዓርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም.፤ በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ)

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁት ቁጥር 133 ደርሷል

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 1, 2020)፦ የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በ24 ሰዓት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው 913 ሰዎች ውስጥ፤ ሁለቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ በመገኘታቸው፤ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 133 መድረሱን ሲያመላክት፤ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ተይዘው ከነበሩት ታማሚዎች ውስጥ በሕክምና ላይ ከሚገኙት ይልቅ ያገገሙት ቁጥር በልጧል።

ዛሬ ዓርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. የወጣው የጤና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመላክተው፤ በ24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ ምርመራ የተገኙት ሁለቱ የቫይረሱ ተጠቂዎች የ20 እና የ25 ዓመት ወንድ ወጣቶች ናቸው።

የ25 ዓመቱ ወጣት ከኬንያ የተመለሰና በሞያሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ ሲሆን፤ የ20 ዓመቱ ወጣት ደግሞ ከፑንትላድ የተመለሰና በጅጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።

በዛሬው ሪፖርት እስከ አሁን በአገሪቱ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 18,754 መድረሱን አመልክቷል። በ24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ አዲስ ሰባት ሰዎች በማገገማቸው፤ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 66 ደርሷል። ይህም በአሁኑ ወቅት በለይቶ ማቆያው ሕክምና ውስጥ ከሚገኙት 62 ታካሚዎች አንጻር ያገገሙት ታማሚዎች ቁጥር በልጦ መገኘቱን ነው።

በአገሪቱ በቫይረሱ ከተያዙት 133 ሰዎች ውስጥ፤ 3ቱ ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ 2ቱ ወደ አገራቸው የተመለሱ ሲሆን፣ 62ቱ በለይቶ ሕክምና ውስጥ ያሉ፣ 66ቱ ደግሞ ያገገሙ ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ