3ዲ (3D) ኮሮና ቫይረስ በምስል (© istock.com/Dr_Microbe)

3ዲ (3D) ኮሮና ቫይረስ በምስል (© istock.com/Dr_Microbe)

በ24 ሰዓት ውስጥ 25 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 7, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱ ከተገለጸበት መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ወዲህ በብዙዎች ዘንድ ድንጋጤ የፈጠረው ዛሬ የተደረገው ሪፖርት ነው ማለት ይቻላል።

ይህም በ24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ 25 አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸውን የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታውቋል። በዚህ መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 187 የደረሰ መኾኑን አመልክቷል።

ትናንት በ24 ሰዓታት ውስጥ 17 አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የትናንቱ መረጃ በ24 ሰዓት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተጠቂ መገኘቱን ያመላከተ ቢሆንም፤ የዛሬው ግን በአንድ ቀን 25 መድረሱ በዙዎችን ሊያስደነግጥ ችሏል።

በቀላል ስሌት በሰዓት ውስጥ አንድ ሰው በቫይረሱ መያዙን የሚያሳይ ስለመኾኑ የሚያመላክት ከመኾኑ አንጻር፤ ዜጎች እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የሁኔታውን አሳሳቢነት የጠቆመ ኾኗል።

የዛሬውን ሪፖርት የበለጠ አስደንጋጭ ያደረገው ደግሞ፤ ከ25ቱ ውስጥ 19ኙ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸውና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ኾኖ መገኘቱ ነው።

በ24 ሰዓት ውስጥ 1,843 የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፤ ከ25ቱ ሦስቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ሲኖራቸው፣ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ የውጭ ጉዞ ያላቸው ስለመኾኑ ተገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ