This illustration, created at the Centers for Disease Control and Prevention (CDC)

ኮቪድ 19 (COVID-19): ኮሮና ቫይረስን በምስል ለማሳየት በበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል (CDC) የተሠራጨ

ይህም በአንድ ቀን ቫይረሱ የተገኘባቸውን 29 አድርሶታል

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 7, 2020)፦ በዛሬው ዕለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 25 ግለሰቦች በተጨማሪ፤ በትግራይ ክልልም አራት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች መገኘታቸውን የትግራይ ጤና ቢሮ በማስታወቁ፤ ባለፉት 24 ሰዓታት በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 29 መድረሱ ታውቋል።

ከሰዓት በፊት በወጣ ሪፖርት፤ ጤና ሚኒስቴር 25 ተጠቂዎች መገኘታቸውን ከገለጸ በኋላ፤ ተጨማሪ አራት ሰዎች በትግራይ መገኘታቸው ሪፖርት በመደረጉ፤ ቫይረሱ በአብዛኞቹ ክልሎች መገኘቱን አመልክቷል። በዚህ መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 191 ደርሷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ