አብን

አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)

ምርጫ እስኪደረግ አሁን ያለው መንግሥት መቀጠሉ አንጻራዊ መፍትሔ ነው ብሏል

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 7, 2020)፦ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ኢትዮጵያ አሁን ለገባችበት ፖለቲካዊ ቀውስ አዲስ የሽግግር መንግሥት መፍትሔ ይኾናል የሚል እምነት እንደሌለው አስታወቀ።

ንቅናቄው ሚያዝያ 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም. የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ካደረገ በኋላ ዛሬ ሚያዝያ 29 ቀን ባወጣው መግለጫ፤ አሁን ባለው ሁኔታ የሽግግር መንግሥት መፍትሔ አለመኾኑንና ከዚህ ይልቅ የተወሰነ የሽግግር ጊዜ መፍጠር የተሻለ አማራጭ መኾኑን እንደሚገነዘብ ገልጿል።

አብን ከዚህ ቀደም ሲያራምድ ከነበረው አመለካከት ለየት ባለ ሁኔታ አቋሙን በገለጸበት በዛሬው መግለጫው፤ የሽግግር ጊዜ አስፈላጊነት ላይ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችና ተቋማት ላቀረቧቸው አማራጭ ሐሳቦች ክብር ያለው ቢኾንም፤ አሁን ለገባንበት ፖለቲካዊ ቀውስ አዲስ የሽግግር መንግሥት አስፈላጊነት ላይ እንደማያምን አመልክቷል።

በዛሬው መግለጫ በሁለቱ ቀናት አስቸኳይ ስብሰባ የአማራ ሕዝብን ወቅታዊ አቋምና ዘላቂ ጥቅሞችን፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ኃይሎች ፍላጎቶችን እና የቀረቡ አማራጮችን በጽሞና በመመርመር ድምዳሜ ላይ የደረሰባቸውን ጉዳዮችም አካትቷል።

በተለይ ላለፉት ሁለት ዓመታት መንግሥት መሩ የለውጥ ሒደት የከሸፈና የማይሠራ እንደነበር ብንረዳም፤ ምርጫው እስኪካሔድ ድረስ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት መቆየትና የሽግግር ሒደቱን መምራት ለሕዝብና ለአገር ካሉት አማራጮች በአንፃራዊነት የተሻለ ነው ብሎ አቋም መያዙም ተጠቅሷል። የአብንን ሙሉ መግለጫ አስነብበኝ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ