Total coronavirus cases in Ethiopia, May 23, 2020

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ (ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2012 ዓ.ም.፤ በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ)

ዛሬ በኢትዮጵያ 61 ተጠቂዎች ሪፖርት የተደረገበት ቀን ኾኗል
ከ61ዱ 45ቱ ከአዲስ አበባ ናቸው

ኢዛ (ቅዳሜ ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 23, 2020)፦ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ጎልቶ የታየባቸው አካባቢዎች የእንቅስቃሴ ገደብ ሊጣል እንደሚችል ተገልጿል።

ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. በአንድ ቀን 61 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተገለጸ በኋላ የጤና ሚኒስትሯ እንዳስታወቁት፤ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ጎልቶ በሚታይባቸው ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ላይ የእንቅስቃሴው ገደብ ሊጣል እንደሚችል ጠቁመዋል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ የሰጠው የአዲስ አበባ ጤና ቢሮም ችግሩ ከፍቶ በታየባቸው የከተማ ክፍሎች የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል መታሰቡንና ገደቡን ለተጣል የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መኾኑን አስረድተዋል።

እስከ አሁን በአዲስ አበባ ከተማ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በአጠቃላይ በአገሪቱ በቫይረሱ ከተጠቁት 494 ሰዎች ውስጥ 62 በመቶውን የሚይዝ ነው። ይህም ከ494ቱ ሰዎች ውስጥ 304ቱ በአዲስ አበባ በመኾናቸው ነው።

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የቫይረሱ ተጠቂዎች ከተገኙባቸው አንዱ ልደታ ክፍለ ከተማ ሲሆን፤ በዚህ ክፍለ ከተማ 104 የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸው የታወቀ ሲሆን፤ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደግሞ 28 የቫይረሱ ተጠቂዎች እንደተገኙ ተገልጿል።

በዛሬው የጤና ሚኒስትሯ መግለጫ እነዚህ ሁለት ክፍለ ከተሞች ይጠቀሱ እንጂ፤ ወረርሽኙ በአሥሩም ክፍለ ከተሞ ተገኝቷል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸው በተገለጸበት በዛሬው ዕለት ከ61ዱ 45ቱ ከአዲስ አበባ የተገኙ ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!