በኦሮሞ ተወላጆች ላይ እስራቱ ቀጥሏል

Ethiopia Zare (አርብ መጋቢት 16 ቀን 2003 ዓ.ም. March 25, 2011)፦ ከእረፍት በኋላ ወደ ትምህርት ገበታቸው ለተመለሱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰኞ ጠዋት የተቃውሞ ሰልፍ እንዲወጡ የሚጠይቅ በራሪ ጽሁፍ በግቢው ውስጥ መበተኑን ምንጮች ገለጹ።

 

ህዝባዊ ጥያቄዎችንና የመብት በከበርን በማንሳት በተለያዩ አገዛዞች ላይ የተቃውሞ ጥሪ በማሰማት የሚታወቀው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስድስት ኪሎ ካምፓስ ተማሪዎች በሰሜን አፍሪካ አገራት የሚካሄደውን ህዝባዊ ቁጣ ተከትሎ የተዘጋጁ የጥሪ ወረቀቶች በግቢው ውስጥ እየተሰራጩ መሆናቸው ተጠቁሟል።

 

ከስፍራው የደረሰን ጥቆማ እንደሚያስረዳው የተበተኑት የጥሪ በራሪ ጽሁፎች ማን እንዳሰራጨው የታወቀ ነገር ባይኖረውም የአመጽ ጥሪው በግቢው ውስጥ አለመረጋጋት መፍጠሩን ምስክሮች ገልጸዋል።

 

ጥሪው በመጨው ሰኞ መጋቢት 19 ቀን ጠዋት ተማሪዎች ለተቃውሞ እንዲወጡ የሚጠይቅ መሆኑ የታወቀ ሲሆን በአብዛኛው ተማሪ ወረቀቶቹን ሲቀባበል መታየቱን ለመረዳት ችለናል።

 

በተያያዘ ዜና በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች አመጽ ለማስነሳት ከስብርተኞች ጋር አሲራችኋል በሚል በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች በየእስር ቤቱ እየተጣሉ መሆኑንና በተለይ በሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚታወቁ የኦፍዴንና የኦብኮ አባላት በእንግልት ላይ መሆናቸው ታውቋል።

 

በኦሮሚያ ክልል ቤት ለቤት አሰሳ እተደረገ ሲሆን በየወረዳዎችና ቀበሌዎች ዝና ያላቸውና ባለሀብት የሆኑ፣ መንግስትን ይቃወማሉ ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች የእስሩ የመጀመሪያ ተጠቂ እንደሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።

 

በነቀምት፣ በናዝሬት፣ በአዲስ አበባና በአርሲ ነገሌ አካባቢዎች ወከባውና እንግልቱ እየተባባሰ ሲሆን በአርሲ ነገሌ አቶ አበበ ኃብተማሪያም፣ አቶ ባንካና አቶ ዮሴፍ የተባሉ ታዋቂ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ታስረው መጀመሪያ ወደ ሻሸመኔ ቀጥሎም ወደ ማእከላዊ ተወስደው መታሰራቸውና ማንም ሊጎበኛቸው እንዳልቻለ ታውቋል። አቶ ዮሴፍ በአርሲ ነገሌ የታወቁ ባለሀብትና ደፋር እንደነበሩ የሚነገርላቸው ከመሆኑም በላይ በተደጋጋሚ የዚህ እና የዚያ ድርጅት አባል ነህ በመባል ይታሰሩ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸው በየሰበብ አስባቡ በድካም ያፈሩትን ንብረት ለመቀማት የአካባቢው ባለስልጣናት ያንገላቷቸው እንደነበር እማኞች አረጋግጠዋል።

 

በአርሲ ነገሌ ቀድሞ ኦብኮ የነበረው የፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ድርጅት አባልና በ2005 ምርጫ የህዝብ ተወካይ ምክርቤት አሸናፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ አዳነ ከምርጫው በኋላ በኦህዴድ ካድሬዎች ትፈለጋለህ ተብለው ተወስደው በጥኢት ተደብድበው በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውና የገደሏቸውም ሰዎች በሹመት ወደሌላ አካባቢ እንደተዛዉ ይታወሳል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ