3ዲ (3D) ኮሮና ቫይረስ በምስል (© istock.com/Dr_Microbe)

3ዲ (3D) ኮሮና ቫይረስ በምስል (© istock.com/Dr_Microbe)

በአንድ ቀን 88 አዳዲስ ተጠቂዎች ተገኙ
55ቱ የውጭ ጉዞ ታሪክም ኾነ ንክኪ የሌላቸው ናቸው

ኢዛ (እሁድ ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 24, 2020)፦ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስጊ መኾኑን የሚያመለክትና በአንድ ቀን ብቻ 88 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የዛሬው የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ይፋ አደረገ። በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 582 ደርሷል።

ዛሬ እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም. የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት በአገሪቱ በአንድ ቀን 88 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው 4,048 ሰዎች ተመርምረው ነው።

ከስምንት እስከ 75 ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ከእነዚህ አዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች ውስጥ 73ቱ ከአዲስ አበባ የተገኙ ናቸው። ስምንቱ ደግሞ ከትግራይ ክልል የተገኙ መኾኑን የጤና ሚኒስቴር ሲያስታውቅ ቀሪዎቹ ደግሞ አራት ከኦሮሚያ፣ አንድ ከሐረሪ ክልል፣ ሁለት ሰዎች ደግሞ የውጭ አገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው የድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪዎች ናቸው።

በሪፖርቱ መሠረት ከ88ቱ ተጠቂዎች ውስጥ 13ቱ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው። በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግነኙነት ያላቸው ደግሞ 20 ናቸው። ቀሪዎቹ 55ቱ ግን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸውና የውጭ የጉዞ ታሪክ ያልነበራቸው ኾነው ተገኝተዋል። ይህም በዕለቱ ከተመዘገበው የበሽተኞች ቁጥር የበለጠው የውጭ ጉዞ ታሪክ የሌላቸውና በሽታው ካለበት ሰው ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ተጠቂዎች በእጅጉ መበራከታቸውን ከማሳየቱም በላይ፤ ወረርሽኙ በኢትዮጵያ እጅግ አስጊ ሁኔታ ላይ መድረሱን አመልክቷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!