Hachalu Hundessa

አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ

ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ ሴት ነች

ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 2, 2020)፦ በአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው የተያዙት ሦስት ሰዎች ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ ሴት ነች።

ፖሊስ በእነዚሁ ሁለት ወንዶችና አንድ ሴት ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀባቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ለፖሊስ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ መስጠቱ ታውቁል።

አርቲስት ሐጫሉ በተገደለ ማግሥት ማክሰኞ ሰኔ 23 ቀን የፌዴራሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንዳሻው ጣሰው በሰጡት መግለጫ፤ አርቲስቱ መኪናው አቁሞ ወርዶ እንደነበርና፤ ተመልሶ ወደ መኪናው ከገባ በኋላ ተጠርጣሪዎቹ የመኪናውን በር በመክፈት በጥይት እንደመቱት ገልጸዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ