Hachalu Hundessa's funeral, 2nd July 2020

በሠላሳ ስድስት ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ የተፈጸመው በአምቦ ነው

ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 2, 2020)፦ ባለፈው ሰኞ በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ ያለፈው የታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በተወለደበት አምቦ ከተማ በሚገኘው ገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያ ተፈጸመ።

የአርቲስቱ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት ደግሞ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም የተከናወነ ሲሆን፤ ከጸጥታ ሥጋት ጋር በተገናኘ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የታደሙት ሰዎች ቁጥር አነስተኛ እንደነበር ተገልጿል።

በትናንትናው ዕለት ደግሞ በፖሊሶችና በወጣቶች መኻል በተፈጠረ ግጭት የ48 ዓመት ዕድሜ ያለው የአርቲስት ሐጫሉ የአጎት ልጅ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል።

አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት የነበረ ሲሆን፤ የ36 ዓመት ወጣት ነበር። የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል በአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን በድጋሚ እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለዘመድ አዝማዶቹ፣ ለወዳጆቹ፣ ለአፍቃሪዎቹና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ