Total coronavirus cases in Ethiopia, August 15, 2020

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ (ቅዳሜ ነኀሴ 9 ቀን 2012 ዓ.ም.)

በቀን የመመርመር አቅም ከ22 ሺህ በላይ ኾኗል
በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 509 ከፍ ብሏል

ኢዛ (ቅዳሜ ነኀሴ ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 15, 2020)፦ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ22,252 ሰዎች የኮቪድ 19 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው፤ 1,652 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መኾናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዛሬው ዕለት (ቅዳሜ ነኀሴ 9 ቀን 2012 ዓ.ም.) ይፋ በተደረገው ሪፖርት መሠረት በ24 ሰዓታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተመርማሪዎች የተስተናገዱበት ነው።

ከእነዚህ ተመርማሪዎች ውስጥ የተገኙት የቫይረሱ ተጠቂዎች በአንድ ቀን ከፍተኛ ኾኖ የተመዘገበበት መኾኑንም ያመላከተ ኾኗል።

ከ1,652 ተጠቂዎች ውስጥ 972 የሚኾኑት ከአዲስ አበባ መኾናቸው ታውቋል። ከፍተኛ ቁጥር ከተመዘገበበት ከዛሬው የምርመራ ውጤት ባሻገር 17 ሰዎች በበሽታው ሕይወታቸው አልፏል። 377 ሰዎችም ያገገሙ ሲሆን፤ 199 ሰዎች ደግሞ በጽኑ የታመሙ ናቸው ተብሏል።

እስከዛሬው ማምሻ ድረስ በአጠቃላይ የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች 589,694 ደርሷል። አጠቃላይ በኢትዮጵያ በበሽታው መያዛቸው ሪፖርት የተደርገው ደግሞ 28,894 ሲሆን፤ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ወደ 509 ከፍ ብሏል። ከበሽታው ያገገሙት ደግሞ 12,037 ስለመድረሱ የዛሬው የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያስረዳል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ