Jawar Mohammed (L), Bekele Gerba (R)

አቶ ጃዋር መሐመድ (በግራ) እና አቶ በቀለ ገርባ (በቀኝ)

ምክንያቱ አቶ ጃዋር በመታመማቸው ነው

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 17, 2020)፦ አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች በተከሰሱበት መዝገብ ዛሬ ሰኞ ነኀሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ሊሰማ የነበረው የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሳይሰማ ቀረ። በዚህ መዝገብ ከተካተቱት ተጠርጣሪዎች ስድስቱ በኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሳይሰሙ የቀሩት፤ አቶ ጃዋር መሐመድ መታመማቸውን በመግለጻቸው ነው።

ፍርድ ቤቱም ሁኔታውን በመገንዘብ የምስክሮችን ቃል ከመስማቱ በፊት እንዲቋረጥ ማድረጉንም ለማወቅ ተችሏል።

በዛሬው የፍርድ ቤቱ ውሎ ከአስራ አራቱ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት የቀረቡት ስምንቱ ብቻ ሲሆኑ፤ የተቀሩት ስድስቱ ያልቀረቡት በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ከመባሉ ጋር ተያይዞ አለመቅረባቸውን ለመገንዘብ ተችሏል። አቶ ጃዋር በግል ሕክምና ተቋም እንዲታከሙ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግን ምስክሮች ለመስማት ለነኀሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ተቀጥሯል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ