የኢትዮጵያ የብር ኖቶች ተቀየሩ
አዲሶቹ የብር ኖቶች
ለመጀመሪያ ጊዜ የ200 ብር ኖት ወጥቷል
(ኢዛ ሰኞ ፬ መስከረም ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 14, 2020)፦ የኢትዮጵያ መገበያያ ገንዘብ የብር ኖቶች ስለመቀየራቸው በይፋ ተነገረ። ሁሉም የብር ኖቶች ከዛሬ ጀምሮ መቀየሩን ይፋ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ናቸው።
የአሥር፣ የሃምሳ እና የመቶ ብር ኖቶች ከመቀየራቸው ባሻገር የ200 ብር ኖት ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ተደርጓል። የአምስት ብር ኖት ደግሞ በቅርቡ ወደ ሣንቲም እንደሚቀየር ታውቋል።
እስካሁን የነበረው ገንዘብ ላለፉት 20 ዓመታት ሲያገለግል ነበር። (ኢዛ)



