የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ምርጫ ቦርድና ኮሮና ቫይረስ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ምርጫ ቦርድና ኮሮና ቫይረስ

ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችል ውሳኔ ነገ ይወሰናል
በኮቪድ 19 ምክንያት የተዘጉ ድንበሮች ይከፈታሉ

ኢዛ (ማክሰኞ መስከረም ፲፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 22, 2020)፦ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ሳይካሔድ የቀረውን ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ (ምርጫ 2012) እንዲካሔድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።

ምክር ቤት ምርጫው እንዲካሔድ ውሳኔውን ያሳለፈው በአንድ ተቃውሞ፣ በስምንት ድምፀ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ ነው።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የተሻለ መረጃ መኖሩንና ምርጫውን በጥንቃቄ ማካሔድ እንደሚቻል የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባለፈው ዓርብ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡትን ምክረ ሐሳብ ተከትሎ የተወሰነ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስቀጠል ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፤ በነገው ዕለት ትምህርት የሚጀመርበት ቀን በይፋ ይነገራል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህም ሌላ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል አገሪቱ ዘግታቸው የነበሩ ድንበሮችዋን እንደምትከፍትም ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!