Lidetu Ayalew (Photo: Addis Fortune)

አቶ ልደቱ አያሌው

የተከሰሱበትን ጉዳይ ለማየት ፍርድ ቤቱ ለመስከረም 20 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል

ኢዛ (ማክሰኞ መስከረም ፲፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 22, 2020)፦ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው የጠየቁትን ዋስትና በመፍቀድ በ100 ሺህ ብር አስይዘው እንዲፈቱ ወሰነ። ነገ ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አቶ ልደቱ በጦር መሣሪያ አስተዳደር አዋጆችን በመተላለፍ በሕገወጥ መንገድ የጦር መሣሪያ በመያዝ በተከሰሱበት ወንጀል ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ሕመምተኛ በመኾናቸው፤ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀው፤ ይህ ጥያቄያቸው በዛሬው (ማክሰኞ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም.) የፍርድ ቤት ችሎት እንዲታይ ቀጠሮ ተይዞ ነበር።

በዛሬው ችሎት ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄያቸውን መርምሮ በአንድ መቶ ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ፈቅዷል። ከእስር የሚፈቱበት ትእዛዝ በዛሬው ዕለት የወጣ ቢኾንም፤ የሥራ ሰዓት በማለፉ በእስር እንዲቆዩ ተደርገዋል።

የተከሰሱበትን ጉዳይ ለመመልከትም ለመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ