20210302 adwa

አቶ ጌታቸው ረዳ እና ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

አቶ ጌታቸው ረዳ (ግራ) እና የቀድሞ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ቀኝ)

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በተለያዩ ወንጀሎች ይፈልጋቸዋል

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 12, 2020)፦ የቀድሞ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ 38 የሚኾኑ የሕወሓት አባላትና ሌሎች ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ተወስኗል።

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት እነዚህ ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ጸድቋል።

ዶ/ር ደብረጽዮንን ጨምሮ በሕወሓት ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነት ላይ ሲያገለግሉ ከቆዩት ውስጥ አቶ አስመላሽ ወልደሰንበት፣ አቶ አባይ ፀሐዬ፣ ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ፣ አቶ ጊታቸው ረዳ፣ አቶ አጽብሃ አረጋዊ፣ አቶ ገብረእግዚአብሔር አርኣያ ተጠቅሰዋል።

የእነዚህ ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ የተላለፈው ውሳኔ ግለሰቦቹ በተጠረጠሩበት ወንጀሎች የጦር መሣሪያ ይዞ በማመጽ፣ የአገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች በዋና አድራጊነት ተጠያቂ ለማድረግ ነው።

በዛሬው የምክር ቤቱ ውሳኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአባልነት ሲያገለግሉ የቆዩትና ዛሬ የመከሰስ መብታቸው የተነሳብቸው ግለሰቦች ወንበራቸውን ይዘው በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ቢጠየቁም፤ እንደፓርቲ ወስነው የወጡ በመኾኑ እንዲሁም በቅርቡ በመከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት እንዲፈጸም እንደፓርቲ የወሰኑ በመኾኑ ፓርቲው (ሕወሓት) ተጠያቂ እንደሚኾንም ተገልጿል።

ያለመከሰስ መብታቸው ከተነሳባቸው የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ግለሰቦች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው። (ኢዛ)

1. ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
2. አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ
3. አቶ አባይ ፀሐዬ
4. አምባሳደር ዶክተር አዲስዓለም ባሌማ
5. አቶ ጌታቸው ረዳ
6. አቶ አጽብሃ አረጋዊ
7. አቶ ታደሰ ኃይሌ
8. ዶክተር መብራቱ መለስ
9. ወ/ሮ ለምለም ሀድጉ
10. አቶ ገብረእግዚአብሄር አርኣያ
11. አቶ ሀለፎም ግደይ
12. አቶ ሀዱሽ አዛነው
13. ወይዘሮ መብራት ገብረጊዮርጊስ
14. ወይዘሮ ሙሉ ገብረእግዚአብሔር
15. ወይዘሪት ልዕልቲ ጸጋዬ
16. ወይዘሮ ማሚት ተስፋይ
17. ወይዘሮ ማና አብርሃ
18. አቶ ካላዩ ገ/ሕይወት
19. አቶ ጌዲዮን ኃ/ሥላሴ
20. መምህር በርሄ ዝግታ
21. አቶ ታደለ አሰፋ
22. አቶ ነጋ አሰፋ
23. ወይዘሮ ናፈቁሽ ደሴ
24. ወይዘሮ ሽሻይ ኃይለሥላሴ
25. ወይዘሮ አልማዝ አርኣያ
26. ወይዘሮ አሰለፈች በቀለ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!