Mulu Nega

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ - ዶ/ር ሙሉ ነጋ

ዶ/ር ሙሉ ነጋ በክልሉ ያሉ ወጣት አመራሮችን አላግባብ ከኃላፊነታቸው አንስተዋል ተብለው ይታማሉ

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. April 7, 2021)፦ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የጸደቀውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እየመሩ ያሉት ዶ/ር ሙሉ ነጋ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የተነገረ ቢኾንም፤ እሳቸው ግን በሥራ ላይ እንደሚገኙና ከኃላፊነታቸው ስለመነሳታቸው እንደማያውቁ መግለጻቸው ተነገረ። ተሰማ። ዶ/ር ሙሉ በክልሉ ያሉ ወጣት አመራሮችን ከኃላፊነታቸው አንስተዋል ተብለው ይታማሉ።

ዶክተር ሙሉ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኾነው በተሾሙበት ወቅት የክልሉን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት የሚመሩ ኃላፊዎችን የመሰየም ሥልጣን የተሰጣቸው በመኾኑ፤ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጭምር ግለሰቦችን በመምረጥ ኃላፊነት ሰጥተው መሾማቸው ይታወሳል።

ዶክተር ሙሉ ነጋ በተለይ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ያሉ ወጣት አመራሮችን ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ በማድረግ ያልተገባ ተግባር ፈጽመዋል እየተባሉ ይታማሉ።

ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል ተብሎ የተናፈሰው ወሬ ሐሰት መኾኑን የገለጹት ዶ/ር ሙሉ ነጋ፤ እሳቸው በሥራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙ እና ከኃላፊነት ስለመነሳታቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና፤ ከአንድ ሳምንት በፊት የመቀሌ ከተማ ከንቲባ በመኾን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አታክልቲ ኃይለሥላሴ ከኃላፊነታቸው የተነሱ መኾኑ የሚታወስ ሲሆን፤ ከኃላፊነታቸው ከመነሳታቸው በፊት የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል ተብሎ ነበር።

በአቶ አታክልቲ ከኃፊነት መነሳት ጋር ተያይዞ ዶ/ር ሙሉ ነጋ አቶ አታክልቲ ከኃላፊነታቸው የተነሱት በሥራ ግምገማ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

የዓረናው አቶ አምዶም ገብረሥላሴም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊነታቸው ከሦስት ሳምንት በፊት መነሳታቸው ይታወቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ