President Abdul Fattah al-Sisi

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ

ለማስጠንቀቅም ዳድተዋል

ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፳፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 30, 2021)፦ በታላቁ ህዳሴ ግድብና በዓባይ ውኃ አጠቃቀም ዙሪያ ድምፃቸው ብዙም የማይሰማው የግብጹ አብዱል ፈታህ አልሲሲ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክት አስተላልፈዋል።

ይህ የፕሬዝዳንቱ መልእክት በአሶሺየት ፕሬስ (AP) በኩል የቀረበ ዘገባ ሲሆን፤ በዓባይ ወንዝ ላይ ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ በአካባቢው የማይገመት አለመረጋጋትን ይፈጥራል በማለት መናገራቸውን የሚያመለክት ነው።

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ አገራቸው ግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለአሥር ዓመታት ስለመደራደራቸው አስታውሰው፤ እስካሁን ሁነኛ ስምምነት ላይ ያለመደርሱን አክለዋል ተናግረዋል።

በግድቡ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት የዛሬው አንደበታቸው፤ ግብጽ ከዓባይ ውኃ ጠብታ እንዲነካባት ያለመሻትዋን የሚያመለክት ብቻ ሳይኾን፤ ከውኃው አንድም ጠብታ መውሰድ አይፈቀድም የሚል ማሰሪያ ቃል ከአንደበታቸው ወጥቷል።

ይህ ከኾነ አካባቢው የትርምስ ቀጠና እንደሚይኾን ለማስጠንቀቅ የሞከሩት አልሲሲ፤ ከዓባይ ውኃ ግብጽ ያላትን ድርሻ መንካት፤ ቀይ መስመር ማለፍ የሚቆጠር ስለመኾኑም በዛሬው ገለጻቸው አመልክተዋል።

እንዲህ ባለው ደረጃ የማስጠንቀቂያ ያህል ከተናገሩ በኋላ፤ እንደው ነገሩን ነው እንጂ ማንንም ማስፈራራታቸው ስላለመኾኑ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ማንንም አላስፈራራንም፤ አሁንም ለማንም ማስጠንቀቂያ እየሰጠን አይደለም ማለታቸውን ይኸው ዘገባ አመልክቷል።

ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበትን 10ኛ ዓመት ባለፈው ሳምንት ያከበረች ሲሆን፤ ግንባታው አሁን ላይ 79 በመቶ መድረሱን፤ ሁለተኛው ግድቡን የመሙላት ሒደት በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንደምትፈጽም አስታውቃለች። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ