ጄኔራል ባጫ ጦሩ ከትግራይ የወጣው የውጭ ሥጋት ስላለ፣ ለዚያ መዘጋጀት ስላለበት ነው አሉ
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን (በግራ) እና ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ (በቀኝ)
“ሰብአዊነት የተላበሰ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው” አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 30, 2021)፦ በትግራይ ክልል በተናጠል የታወጀው የተኩስ አቁም ኢትዮጵያ ለተደቀነባት የውጭ ሥጋት መዘጋጀት ያለባት በመኾኑ ጭምር ስለመወሰኑ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ገለጹ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄኔራል ባጫ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳከሉት፤ አሁን ኢትዮጵያ ሥጋት የውጭ አገራት ጣልቃ ገብነት በመኾኑ፤ ለዚህ መዘጋጀት አስፈላጊ እና አስገዳጅ በመኾኑ የመከላከያ ኃይሉ ከትግራይ እንዲወጣ ተወስኗል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው በመንግሥት በኩል የተወሰደው የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ሰብአዊነት የተላበሰ ፖለቲካዊ ውሳኔ መኾኑን ጠቅሰው፤ የትግራይ አርሶ አደሮች ወደ እርሻ እንዲገቡ ታስቦ መኾኑን አስረድተዋል። (ኢዛ)



