ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በስዊድን ቆይታ አደረጉ

Dr. Negasso Gidada ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳየሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ ኃላፊዎችንና ኢትዮጵያውያንን አነጋገሩ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 8 ቀን 2003 ዓ.ም. September 18, 2010)፦ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት፣ የአሁኑ የመድረክ የውጪ ኮሚቴ አባል፣ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ የስዊድን ሾሻል ዲሞክራት ፓርቲ ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ካለፈው ረቡዕ ጳጉሜን 3 ቀን ጀምረው በስቶክሆልም በመገኘት እንቁጣጣሽን ከኢትዮጵያውያን ጋር አብረው አሳለፉ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስቶክሆልም በአይነቱ ልዩ መንፈሣዊ ጉባዔ ተካሄደ

ፍቅረሥላሴ አቢይ (ከስቶክሆልም)

በሰሜን አውሮፓ ሀገረ ስብከት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ፤ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተዘጋጅቶ የነበረው የሦስት ቀን ጉባዔ በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ። … (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

ብርቱካንን እንጂ ዓላማውን ማሰር አይቻልም!!!

በስዊድን የተካሄደ ብርቱካን ትፈታ ህዝባዊ ስብሰባ

ስሜነህ ታምራት - ከስዊድን

Stockholm 2010, 02, 20 Free Birtukan!

የመሰብሰቢያ አዳራሹ በኢትዮጵያና በስዊድን ሰንደቅ ዓላማዎች ከብርቱካን ፎቶግራፍ ጋር ተውበዋል። ወደ ውስጡ ሲገባ ብርቱካን ቃሌ ብላ ከሰጠችው የተወሰደው የእውነተኛ ምስክርነት ንግግርና ለእስር ምክንያት ተብሎ የቀረበው በስዊድን ጉብኝትዋ ስለምህረቱ አፈፃፀም ያደረገችው ንግግር ይሰማል። በተለያዩ ሀገሮች ከህዝብ ጋር ስትወያይ ”ባገራችን ሠላም ዲሞክራሲና የሕግ የበላይነት እንዲከበር እኔ በዓላማዬ ፅኑ ነኝ እናንተስ?” በማለት ያስተላለፈችውና በማንኛውም ሐቀኛ ዜጋ ዘወትር የማይረሳው የቆራጥነት መንፈሧ በአየር ላይ ይታያል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የከተማ ድሆች ሁኔታ

በቅርቡ ጥናት ያደረጉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ድህነት መባባሱን ነው። በተለይም በመዲናዋ አዲስ አበባ የድህነት ገጽታው በከፍተኛ ፍጥነት ማሻቀቡን ከሚታየውና ከሚሰማው ነገር መረዳት ይቻላል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቃቂ ወንዝ ብክለት

በማግነስ ፍራንክሊን

ሰዎች በአንድ አካባቢ መሥፈር የጀመሩት የወንዝ ተፋሰሶችን ተከትለው ነው። በዋነኝነትም ወንዞች ለሠፈራ ቁልፍ ሚና ነበራቸው፤ ነገር ግን ከንግድ ተቋማት ጋር ሲተሳሰሩ ምን ይፈጠራል? ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአሜሪካ የጦር ዕዝ በሶማሊያ የባህር ላይ ወንበዴዎች

U.S. Navy destroyer USS Howard, left, and the Russian missile frigate Neustrashimy responded to the Somalia coast in response to a pirate hijacking.
“ዩ.ኤስ.ኤስ. ሐዋርድ” የተሰኘችው የዩናይትድ ስቴትስ የአሜሪካ ባህር ኃይል የጦር መርከብ (በግራ)፣ የሩሲያ “ኑስትራሺሚ” የተሰኘችው ሚሳይል ተሸካሚ የጦር መርከብ (በቀኝ) (ፎቶ AP)
አሜሪካ በአፍሪካ የጦር ዕዝ እንዲኖራት ፍላጎት እንዳላት ካስታወቀች ዓመታት ተቆጥረዋል። አሁንም ፍላጎቷ በአብዛኛዎቹ አፍሪካውያን እንደ ትልቅ ስጋት እየታየ ነው። በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ (Africom) አዛዥ ጄኔራል ዊልያም ዋርድ እንደሚገልፁት የአሜሪካ የጦር ዕዝ በአፍሪካ መቋቋሙ ድብቅ አጀንዳ የለውም፤ አሜሪካ በአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብትን በተለይም ዘይትን ለመመዝበር ፍላጎት አላት የሚለውም የተዛባ ነው ብለውታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...