በሜልቦርን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ኢሰብዓዊ ጥቃት ተቃወሙ
Ethiopians protested in Meelbourne. በሜልበርን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ኢሰብዓዊ ጥቃት በመቃወም ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ሚያዝያ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. (April 24, 2015) የሜልበርን ኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲ እና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በሕብረት ባስተባበሩት የተቃውሞ ሰልፍ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር የነበረው ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ ቁጣውን በመረረና እልህና ቁጭት በተንጸባረቀበት መልክ ሲገልጽ አርፍዷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእነብርሃኑ፣ ፍቅረማርምና እየሩሳሌም የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ

ኤልያስ ገብሩ

ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል
‹‹ተጨማሪ ምርመራ ይቀረኛል›› መርማሪ ፖሊስ
‹‹መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› ተጠርጣሪዎች

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚገኙት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ፍርድ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ግሰለቦች የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ

ኤሊያስ ገብሩ

‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም። ኢህአዴግ አሸባሪ ነው። ለሽብር ሀሳቡም ፍላጎቱም የለኝም›› ዳንኤል ሺበሺ

‹‹የተባለውን ለነገር አለማድረጌን ከእኔ በላይ የከሰሰኝ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል›› ሀብታሙ አያሌው

‹‹ለእኔ ብቸኛው አሸባሪ ህወሃት/ኢህአዴግ ነው። እኔ የህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ ነኝ›› አብርሃ ደስታ

‹‹ይሄ 19ኛ ችሎት የጦር ፍርድ ቤት ችሎት እየመሰለ ነው›› የሺዋስ አሰፋ

‹‹ኃይማኖቱንና ማኅበረሰቡን ከሚፈራ ህዝብ ወጥቼ እንዲህ አይነት ተግባር አልፈጽምም›› ባህሩ ታዬ

ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓ.ም፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት እና በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ ያሉ 10 ሰዎች ቀርበው ነበር። መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመቀበል እና ከ1-5ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተከሳሾች በእስር ቤቱ ደረሰብን ብለው ባቀረቡት አቤቱታ ላይ አስተያየት ካላቸው ለመቀበል መሆኑን የችሎቱ የግራ ዳኛ ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” (ሂዩማን ራይት ዎች)

በኢትዮጵያ የመገናኛ-ብዙሃን ነጻነት ላይ የሚፈፀም የመብት ጥሰት እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 2015 ዓ.ም.

ማጠቃለያ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እ.ኤ.አ. በ2010 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ 99.6 በመቶ የፓርላማ መቀመጫን ካሸነፈ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እና መረጃ የማግኘት መብትን በመገደብ በግል መገናኛ-ብዙሃን ላይ እያሳደረ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ አባብሶታል። እ.ኤ.አ. ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ቢያንስ 60 ጋዜጠኞች ሃገር ለቀው የተሰደዱ ሲሆን ሌሎች 19 ጋዜጠኞች ደግሞ በእስር ላይ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእምነት ክህደት ቃል በኃይል አስፈርመዋቸዋል

መዝገቦቹ መልሰው ተቀራረቡ

ጽዮን ግርማ

የሦስቱ ብሎገሮች አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን የሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. የፍርድ ቤት ቀጠሮ

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በስድስቱ ጦማሪያንና በሦስቱን ጋዜጠኞች ላይ የፌደራል ፖሊስ የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቀጠሮ የሚያራዝመውን ሁለት መዝገብ አንዴ ሲያቀራርበው መልሶ ደግሞ ሲያራርቀው ቆይቶ አሁን ደግሞ መዝገቦቹን መልሶ አቀራርቧቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወጣቶቹና - ቅዳሜ

አንዷን ቅዳሜ በፍርድ ቤት
በዛሬው ችሎት ፖሊስ የሃያ ስምንት ቀን የምርምራ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደለት

ጽዮን ግርማ

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና አጥናፉ ብርሃነ Journalist Tesfalem Weldeyes, Zelalem Kibret, journalist Asmamaw H/ghiorgis, journalist Edom Kassaye, Natnael Feleke and Atnaf Berhane

ለአብዛኛው ወጣት አዲስ አበባ ላይ ”ቅዳሜ” ትርጉም አላት። የሣምንቱን የሥራ ቀናት በየፈርጁ ያሳለፈው ኹሉም ወጣት ”ቅዳሜ”ን ደግሞ እንደየምድቡ ይውልባታል። እንደሰማኹት ከኾነ ለዞን ዘጠኝ አባላትና ጓደኞቻቸውም ቅዳሜ ልዩ ቀን ናት። ለወጣቶቹ አብሮነት የጡመራ መድረኩ ቢያግዛቸውም ከዛ በላይ ግን ጓደኝነታቸው ቤተሰባዊነትን ፈጥሮላቸው አብዛኛውን ቅዳሜ እንደየቅርበታቸው አብረው ያሳልፋሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሦስተኛዋን ”እሁድ” - በአራዳ ምድብ ችሎት

ጽዮን ግርማ
ሦስተኛዋን ”እሁድ” - በአራዳ ምድብ ችሎት

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ስድስቱን ጦማሪያንና ሦስቱን ጋዜጠኞች በሰንበት ቀን ለሚሰየም ተረኛ ችሎት መቅጠሩን የተለመደ አድርጎታል። ከቀናት በፊት በሦስቱ ብሎገሮች አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን ላይ በተሰጠው የዐሥራ አራት ቀናት የጊዜ ቀጠሮ መሠረት የቀጠሮው ቀን ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ነበር። ዛሬ በዚህ ፍርድ ቤት ተገኝቼ የነበረውን ሁኔታ መከታተል ባልችልም ምንጮቼ የነገሩኝን ዝርዝር እንዲህ ጽፌዋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሁለት ቀናት ክራሞት በአራዳ ምድብ ችሎት

ጽዮን ግርማ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.(በፋክት መጽሔት የታተመ)
የታሰሩት ስድስቱ ጦማሪያንና (Bloggers) ሦስቱ ጋዜጠኞች 3 jailed journalists and 6 bloggers
ሚያዚያ 17 እና ሚያዚያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር የዋሉት ስድስቱ ጦማሪያንና (Bloggers) ሦስቱ ጋዜጠኞች በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ከታሠሩ ዛሬ ሃያ ሦስተኛ ቀናቸውን ይዘዋል። በእነዚህ ጊዜያት ውስጥም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ሁለት ጊዜ ቀርበዋል። እሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀርቡ ብቻቸውን በመኾኑም የፍርድ ቤቱ ድባብ ምን ይመስል እንደነበር የሚያውቅ አንድም ታዛቢ ሰው አልነበረም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"የሳዑዲ መንግሥት በሕግ ሊጠየቅ ይገባል" በፍሎሪዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

እሁድ ኖቨምበር 24 ቀን 2013 (እ.ኤ.አ.) በፍሎሪዳ ስቴትስ በምትገኘው ታምፓ ቤይ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት በሳዑዲ ዐረቢያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ኢሰብዓዊ በደል ከልብ እንዳስቆጣቸው ገልጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!