በስዊድን ፳ኛው የአውሮፓ ዓመታዊ የስብከተ ወንጌል ጉባዔ በደማቅ ኹኔታ ተጠናቀቀ

ማቴዎስ ዘገየ (ከስዊድን)

ብፁዓን ጳጳሳት
በ፳ኛው በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዓመታዊ ስብከተ ወንጌል ጉባዔ ላይ የተገኙ ብፁዓን ጳጳሳት

በዚህ በያዝነው የአውሮፓውያን በጋ ሐምሌ ወር፣ የሰከነ የሕይወት እንቅስቃሴና የረጋ ጸጥታ የሚታይባት፣ ከአውሮፓ ጽዱ ከተሞች አንዷ የሆነችው የስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም፤ ፳ኛውን በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዓመታዊ ስብከተ ወንጌል ጉባዔን በተሳካ ኹኔታ አስተናገደች።

በመላው አውሮፓ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በየዓመቱ የሚዘጋጀው ይኸው መንፈሳዊ ጉባዔ ከሐምሌ (ጁላይ) ፲፬ እስከ ፲፮ ቀን ፳፻፲፯ እ.ኤ.አ. ድረስ ከተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የመጡ ምዕመናን፣ እንዲሁም ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካና ከካናዳ የመጡ ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት ነበር በተሳካ ኹኔታ የተካኼደው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“አልቅሳችሁ አትቅበሩኝ” የአሰፋ ጫቦ ሥርዓተ ቀብር ተከናወነ

አክሊሉ ሀብተወልድ

Assefa Chabo | አሰፋ ጫቦ
አቶ አሰፋ ጫቦ (፲፱፻፴፮ - ፳፻፱ ዓ.ም. | እ.ኤ.አ. 1944 - 2017)

(ሚያዝያ 27 ቀን 2009 ዓ.ም)፡- ሚያዝያ 27 ታሪካዊ ቀን ናት፤ ከሰባት አስርት ዓመታት በፊት ከፋሺስት ጣሊያን ወረራ በኋላ አገር ነጻነቷን ያወጀችበት ሕዝብ እንደ ሕዝብ ደስ የተሰኘበት ቀን ናት። የዛኔ በስደት የነበሩት ንጉሥ ከስደት መልስ አገራቸው የገቡበት ቀን ነው፤ ዛሬ ግን በደርግ ዘመነ መንግሥት በጽሑፋቸው ለአስር ዓመት ከስድስት ወር በማዕከላዊ ካሳለፉ በኋላ በዘመነ ኢሕአዴግ የ16 ዓመት እስር የተፈረደባቸው። ላለፉት 25 ዓመታት በስደት በአገረ አሜሪካ ሕይወታቸውን የገፉት የሦስት ልጆች እና የዘጠኝ የልጅ ልጆች አባት፤ አገራቸውን ለማቅናት ዕድሜ ዘመናቸውን ሲወጡ ሲወርዱ፤ አገሬን ... አገሬን እያሉ ሞታቸው ከስደት አገር ከወደ ዳላስ የተሰማው አንጋፋው ጎምቱ ጸሐፊ፤ የሕግ ባለሙያ፤ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ፖለቲከኛና ምሁር የአቶ አሰፋ ጫቦ ሥርዓተ ቀብር የተከናወነበት ቀን ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጋምቤላ 18 ተገደሉ፣ ከ22 በላይ ሕጻናት ታፍነው ተወሰዱ

የጋምቤላ ጥቃትና ታፍነው የተወሰዱት ሕጻናት ጉዳይ

Gambela
የሙርሊ ታጣቂዎች ወደ 13 የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል፤ 21 የሚሆኑ ሕጻናት ታፍነው በሞርሊ ተወስደዋል

(ዶቼቬለ) ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን በጎን እና በጆር ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ጎሣ ታጣቂዎች በጣሉት ጥቃት ከአስራ ስምንት ሰዎች በላይ መገደላቸውንና ከ22 በላይ ሕጻናት ታግተው መወሰዳቸውን ተቀማጭነቱን ለንደን ላይ ያደረገው ”አኝዋ ሰርቫይቫል” የተሰኘው ድርጅት ገለፀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የባለሥልጣናቱን ኪስ ነፍስ የሚዘራበት የኢትዮጵያ የስኳር ምርትና ፍላጎት

Sugar factories

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) ስኳር የጫኑ 101 የከባድ ጭነት መኪናዎች አዋሽ ፍተሻ ጣቢያ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ እየተጉላሉ ነው ሲል አገር በዝምታ ተውጣ በትዝብት የምትከታተለውን የስኳር ወሬ ወደ ፊት አምጥቶታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች፤ ፖሊስ እና ሠራዊቱ በህዝብ ላይ አልተኩስም ብለዋል

ወቅታዊ ሪፖርታዥ (ክንፉ አሰፋ)

Addis Ababa joined the protest

በሳምንቱ መግቢያ የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ እና ድርድር እንዲደረግ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። አምስቱ የህወሓት ቁንጮዎች ትዕቢት የተሞላበት ምላሽ ነው የሰጡት። ከድርድር ይልቅ ከህዝብ ጋር ጦርነት መግጠምን መርጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢሬቻ በዓል ላይ ስለነበረው ሁኔታ አንድ የዓይን እማኝ ምስክርነት

ሳሚታ ተፈራ

Irrecha protest, 2nd Oct 2016

እኔና ጓደኛዬ በስልካችን ምስልና ቪዲዮ እየቀረፅን ስለምንጓዝ ጉዟችን ቀርፋፋ ነበር። በምንሄድበት መንገድ የወታደሩ ቁጥር፤ መሣሪያ የደገኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እጅግ ብዙ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ደንበኛ ጦር ሜዳ በሚያስመስል መልኩ በመሬት ታንክ እና በሰማይ ላይ ደግሞ የጦር ተዋጊ ጄት ከ4:00 ሰዓት ጀምሮ በማንዣበብ ህዝቡን ሲያሸብሩ ነበር። እኛም ወደ ሆራ አርሰዲ በተጠጋን ቁጥር የህዝቡ ብዛት እና የህዝብ ጥያቄ የሚያስተጋቡ ዜማዎችና መፈክሮች ጠንከር ባለ መልኩ በዚያ አካባቢ በነበሩ የበዓሉ ታዳሚዎች በሙሉ ይስተጋባ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግ ካባረራቸው አባላቱ ጋር ለእርቅ እየተነጋገረ ነው

EPRDF ኢህአዴግ

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. June 7, 2015)፡- የትግል ታሪኩ ጥንካሬ በገዛ አባላቱ ተጋኖ የሚነገርለት ኢህአዴግ ሥልጣን ይዞ በቆየበት 24 ዓመታት ለህልውናው አስጊ የሆኑ ፈታኝ ጊዚያቶች በተደጋጋሚ አሳልፏል። ከእነዚህ ውስጥ በ1993 ዓ.ም. አመራሩ ለሁለት ተሰንጥቆ በነበረበት ጊዜ የደረሰው ውጣውረድ፣ በቀድሞው ጠ/ሚንስትር ሞት የደረሰው ክፍተት እንዲሁም የ1997ቱ ምርጫ ባስከተለው ህዝባዊ ዓመጽ መሬት ነክቶ የመመለሱ አደጋ የሚጠቀሱ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እረጭ ያለው ምርጫ

Ethiopian election 2015. እረጭ ያለው ምርጫበኢትዮጵያ የተካሄደውን የ2007ቱን ምርጫ አስመልክቶ የቪኦኤ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ ባጠናከረው ዘገባ፣ "አዲስ አበባ ውስጥ ከባነሮቹና እጅግ ከተጋነነው የሙዚቃ ጩኸት በተረፈ አገሪቱ በ90 ሚሊዮን ሕዝብ የተመላች አትመስልም፤ ባልተለመደ ሁኔታ እረጭ ያለ ምርጫ" በማለት የምርጫውን ሁኔታ ገልጦታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሊቢያ በደቡብ አፍሪካና የመን ለተገደሉ ወገኖቻችን በሲድኒ የሻማ ማብራት ሥነሥርዓት ተከናወነ

አቢይ አፈወርቅ
Sydney candlelight vigil. በሊቢያ በደቡብ አፍሪካና የመን ለተገደሉ ወገኖቻችን በሲድኒ የሻማ ማብራት ሥነሥርዓት ተከናወነ

በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ያስቆጣቸው የሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን እሁድ ኤፕሪል 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ የሻማ ማብራት ስርአት አካሂደዋል። በዚህ በኒው ሳውዝ ዌልስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር አስተናባሪነት በተዘጋጀው ሥነሥርዓት ላይ ቁጥራቸው ከ350 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!