ጉምቱው የኪነጥበብ ባለሙያ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ አረፈ

Tesfaye Gessesse

በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አበርክቷል

ኢዛ (ረቡዕ ታኅሣሥ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 16, 2020)፦ አንጋፋው የኪነጥበብ ባለሙያና መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ በ83 ዓመቱ ዛሬ ታኅሣሥ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለአዲስ አበባ የሚሰማው ጉድ ቀጥሏል

Addis Ababa

የተሰረቀው መሬት ከ13 ነጥብ 6 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ ኾኗል
በሕገወጥ መንገድ በተመሠረቱ 64 መንደሮች 6 ነጥብ 8 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ተይዟል

ኢዛ (ረቡዕ ታኅሣሥ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 16, 2020)፦ በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መንገድ የተወረረውን መሬት ከሥር ከሥር በሚደረግ ማጣራት እየተገኘ ያለው መረጃ የከፋ ደረጃ ላይ ስለመድረሱ እየተመላከተ ሲሆን፤ ዛሬ ይፋ በተደረገው መረጃም በሕገወጥ መንገድ የተያዘው መሬት ከ13 ነጥብ 6 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ ደርሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትግራይ ጊዜያዊ ካቢኔ ነገ ሥራ ይጀምራል

Mulu Nega

የመንግሥት ሠራተኞች ሰኞ ሥራ እንዲጀምሩ ጥሪ ተደርጓል
በሥራ ገበታው ላይ ያልተገኘ በፈቃዱ እንደለቀቀ ይቆጠራል

ኢዛ (ቅዳሜ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 12, 2020)፦ የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ከነገ ታኅሣሥ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ሥራ እንደሚገባና ከታኅሣሥ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. በሥራ ገበታው ላይ የማይገኝ ሠራተኛ በገዛ ፈቃዱ ሥራውን እንደለቀቀ የሚቆጠር መኾኑን ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጓድ ፍቅረሥላሴ አረፉ

Fikreselassie Wogderess and Genet Ayele

"ምን ከእንግዲህ ወዲያ የኢትዮጵያን ጠላቶች መጨረሻ ዓየን አይደል እንዴ?” ጓድ ፍቅረሥላሴ በመጨረሻ ሰዓታቸው የተናገሩት

ኢዛ (ቅዳሜ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 12, 2020)፦ በደርግ የአገዛዝ ዘመን ለዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር በመኾን ሲያገለግሉ የነበሩት ጓድ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ማረፋቸው ተሰማ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ተደፍሯል

National Election Board of Ethiopia (NEBE)

የክልሉ ፖሊስ በዋና መሥሪያ ቤቱ ሊፈጸም የነበረውን የእስር ሙከራ አወገዘ

ኢዛ (ቅዳሜ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 12, 2020)፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በዋና መሥሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የፖለቲካ ድርጅት አመራር አባላትን የቤንሻንጉል ክልል ፖሊስ ለማሰር ያደረገውን ሙከራ የቦርዱን ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነት እንደሚጋፋና የድርጊቱን አሳሳቢነት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ድምፂ ወያኔ ስቱዲዮውም ድምፁም ተይዟል

Dimtsi Weyane

መከላከያና ፌዴራል ፖሊስ ድምፂ ወያኔ ስቱዲዮ ውስጥ ናቸው

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 4, 2020)፦ የሕወሓት ቡድን ዋነኛ የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ጣቢያ በመኾን የሚታወቀው የድምፂ ወያኔ ስቱዲዮ ዛሬ ዓርብ ኅዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በአገር መከላከያ እና የፌዴራል ፖሊስ ተቆጣጥሮታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፖለቲከኛና ደራሲ አንዳርጋቸው ጽጌ ለመከላከያ የመቶ ሺህ ብር ቼክ ድጋፍ ሰጡ

ፖለቲከኛ እና ደራሲ አንዳርጋቸው ጽጌ የመቶ ሺህ ብር ቼክ ለመከላከያ ውጭ ግንኙነት ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ቡልቲ ሲያስረክቡ

ሕወሓት በአገር መከላከያ ሠራዊቱ ላይ በተኛበት የፈጸመውን እጅግ አስከፊና አሳዛኝ ጥቃት አውግዘዋል

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 3, 2020)፦ ራሳቸውን ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ያገለሉት ፖለቲከኛ እና ደራሲ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ከአዲሱ መጽሐፋቸው ሽያጭ ገቢ ካገኙት ላይ የአንድ መቶ ሺህ ብር ቼክ ለመከላከያ ሚኒስቴር አበረከቱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተጠባቂው የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ነገ ይጀመራል

Prosperity Party

አጀንዳው ወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ነው

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 3, 2020)፦ በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ የሚጠበቀው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ነገ ዓርብ ኅዳር 25 ቀን ዓ.ም. ይጀምራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርጫ ዙሪያ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር መከሩ

PM Abiy Ahmed held a meeting with Opposition parties and Civic organizations

ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እንዲኾን መግባባት ላይ መደረሱ ተገለጸ
የተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን አመስግነዋል

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 2, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራሮች እና የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች ጋር በቀጣዩ ምርጫ ዙሪያ መወያየታቸውንና ምርጫው ዴሞክራሲያዊ የሚኾንበትን መንገድ በተመለከተ መግባባት ላይ ስለመደረሱ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ፍርድ ቤት ቀረበ

Journalist Dawit Kebede, Awramba Times

ለፖሊስ የ13 ቀን የምርመራ ጊዜ ተሰጠው

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 2, 2020)፦ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የተዛባ መረጃ በማውጣትና ግጭት በመቀስቀስ፣ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ሲንቀሳቀስ እንደነበርና ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወንጀል ተጠርጥሮ ዛሬ ረቡዕ ኅዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!