በመቀሌ ከተማ በመንግሥት የማይታወቅ የጦር መሣሪያ ዴፖ ተገኘ

በመቀሌ የተገኘውና መከላከያና ሰሜን ዕዝ የማያውቁት የጦር መሣሪያ ማከማቻ ዴፖ

በመቀሌ ቤት ለቤት ፍተሻ ተጀምሯል

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 2, 2020)፦ በመቀሌ ከተማ ውስጥ በመንግሥትም ኾነ በሰሜን ዕዝ የማይታወቅና የጁንታው የሕወሓት ቡድን ለጥፋት ሊጠቀምበት የነበረ የጦር መሣሪያ ማከማቻ ዴፖ መገኘቱንና በአገር መከላከያ እጅ መግባቱ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን መቀሌ ገባ

TPLF

ቡድኑ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመኾን ወንጀለኞችን ማደን ጀምሯል

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 2, 2020)፦ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ማምሻውን እንዳስታወቀው የኮሚሽኑ ልዩ የኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን ዛሬ መቀሌ ገብቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ አንዳንድ ከተሞች ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ጀመረ

Ethio Telecom

በአላማጣ ሙሉ ለሙሉ፣ በዳንሻ፣ ተርካን፣ ሑመራ፣ ሽራሮ፣ ማይጸብሪ እና ማይካድራ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 2, 2020)፦ ኢትዮ ቴሌኮምም በትግራይ ክልል የቴሌኮም አገልግሎትን ለማስጀመር እየሠራ መኾኑን አስታውቆ፤ በአሁኑ ወቅትም በአላማጣ ከተማ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ጀምሯል። በሌሎች የክልሉ አካባቢዎችም በከፊል አገልግሎት ስለመጀመሩ ያስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም፤ በከፊል አገልግሎት ከተጀመረባቸው ከተሞች ውስጥ ዳንሻ፣ ተርካን፣ ሑመራ፣ ሽራሮ፣ ማይጸብሪ እና ማይካድራ ይገኙበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ ክልል የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች እንዲንቀሳቀሱ ተፈቀደ

National Bank of Ethiopia

በክልሉ የሚገኙ ከ600 በላይ የባንክ ቅርንጫፎች የሚከፈቱበት ሁኔታ እየታየ ነው

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 2, 2020)፦ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች አካውንት ከፍተው፤ ከትግራይ ክልል ውጭ አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነስቶ፤ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል አካውንታቸውን እንዲያንቀሳቅሱ ተፈቀደ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቀድሞው ሚኒስትርና የብአዴን ከፍተኛ አመራር ከአገር እንዳይወጡ ተከለከሉ

Kebede Chane

ለሕወሓት ጁንታ ቡድን ምስጢር በማቀበል ተጠርጥረው ስለመኾኑ እየተነገረ ነው

ኢዛ (ማክሰኞ ኅዳር ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 1, 2020)፦ ከቀድሞ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ የኾኑትና በተለያዩ የመንግሥት የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በመመደብ እስካሁን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ከበደ ጫኔ ከአገር ለመውጣት ያደረጉት ሙከራ በጸጥታ ኃይሎች ተገታ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በልዩ ስብሰባ ለፓርላማ ማብራሪያ ይሰጣሉ

PM Abiy Ahmed

ዋነኛ አጀንዳው ከትግራይ ክልል ሕግ ማስከበር ጋር እንደሚያያዝ ይጠበቃል

ኢዛ (እሁድ ኅዳር ፳ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 29, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተመለከተ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

27 በአገር ክህደት የተጠረጠሩ የጦር መኮንኖች የመያዣ ትእዛዝ ወጣ

Daniel Berhane, Prof Hizkiel Gebissa and Alula Solomon

ዳንኤል ብርሃኔና ከፍተኛ መረጃ በማሰራጨት የተጠረጠሩት 7 ሰዎች ላይም ትእዛዝ ወጥቷል

ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 28, 2020)፦ የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በማሰራጨት የተለዩ ስምንት ግለሰቦችና 27 ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትእዛዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል። ዳንኤል ብርሃኔና አሉላ ሰለሞን ይገኙበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በማይካድራው ጭፍጨፋ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው

Mai-Kadra massacre

የጅምላ መቃብሮች እየተገኙ ነው

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 27, 2020)፦ በአገር ውስጥና በውጭ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጨምሮ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ በብርቱ በተወገዘው የማይካድራው ጭፍጨፋ የሟቾች ቁጥር አሁን ከሚገለጸው ከ600 በላይ እንደሚኾን ማረጋገጫዎች እየተገኙ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መንግሥት የማይካድራውን ጭፍጨፋ አወገዘ

Office of the Prime Minister

ድርጊቱ የሕወሓትን ማንነት ያሳየ ነው

ኢዛ (ማክሰኞ ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 24, 2020)፦ የሕወሓት ቡድን በማይካድራ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በንጹኀን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ጭካኔ የተሞላበት ተግባር ያወገዘው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ዓለምም ይህንን ድርጊት እንዲያወግዝ ጠየቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የብሮድካስት ባለሥልጣን በውጭ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ የወሰደበትን ምክንያት አስታወቀ

Ethiopian Broadcasting Authority

ቢቢሲና ጀርመን ድምፅ አማርኛ፣ አልጀዚራ፣ ሮይተርስና ዊልያም ዳቪሰንን በሚመለከት ማብራሪያ ተሰጥቷል

ኢዛ (ሰኞ ኅዳር ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 23, 2020)፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በቅርቡ በውጭ ሚዲያዎችና ዘጋቢዎች ላይ የወሰዳቸውን እርምጃዎች በዝርዝር የሚያመላክት መግለጫ አወጣ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!