የብሔር ግጭት በኢትዮጵያ ተባብሷል

Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2000 ዓ.ም. March 10,2008) ባለፈው ሣምንት በደቡብ ክልል በተነሳ በጉጂ ኦሮሞ እና አማሮ ኬሌ በተባሉ ብሔረሰቦች መካከል በተነሳ ብጥብጥ ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸውን በአካባቢው ያሉ ምንጮች ገለፁ።

በአካባቢው የሚገኙ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት ከአምስት ቀናት በፊት በአካባቢው በተነሳ ብጥብጥ ሁለቱ ብሔሮች እርስ በርሳቸው በፈጠሩት አለመስማማት ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን የገለፁ ሲሆን፣ ማንም ወደ አካባቢው እንዳይጠጋ መንገድ ተዘግቷል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች በጥቂት ወራት ልዩነት የብሔር ግጭት እየተበራከተ ቢመጣም መንግሥት በጉዳዩ ላይ ርምጃ ሲወስድ አይታይም።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ