አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ማመልከቻውን ለምርጫ ቦርድ አስገባ
ለነገ ተቀጥረዋል
Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2000 ዓ.ም. March 10,2008)፦ በቅንጅቱ ተ/ም/ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሣ የሚመራው ሥራ አስፈፃሚ አዲስ ለሚያቋቁመው ፓርቲ ሥም ከመረጠ በኋላ የፓርቲውን ሕጋዊነት ለማስጠበቅ የሚያስችለውን ፊርማ ለማሰባሰብ የሚያስችለውን ቅፅ እንዲሰጠው በዛሬው ዕለት ለምርጫ ቦርድ አመለከተ።
በቅንጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ይህንኑ ሥራ እንዲያከናውኑ የተመረጡት ኮሚቴዎች በትናንትናው ዕለት "አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ" በሚል ስያሜ የተመረጠውን ፓርቲ ስያሜ በመያዝ ለቦርዱ ማመልከቻ ያስገቡ ሲሆን፣ ማመልከቻውን የተቀበሏቸው የምርጫ ቦርድ የመዝገብ ቤት ሠራተኞች ለነገ ቀጠሮ ሰጥተዋቸዋል።



