Ethiopia Zare (መጋቢት 1 ቀን 2000 ዓ.ም. March 10,2008) "በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አምኖ የነበረው ዲያስፖራ እኔ እውነቱን ስነግረው አምኖ ተፀፀተ" ሲሉ አቶ በድሩ አደም ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለፁ። "ወ/ት ብርቱካን የተመረጠችው ያለምንም ልምድ ኦሮሞና ሴት ስለሆነች ብቻ ነው" ሲሉም ተናግረዋል። አቶ በድሩ "ቅንጅት የጀመራቸውን ሥራዎች ኢህአዴግ ተግባራዊ እያደረጋቸው ነው" ማለታቸውን ተከትሎ ብዙዎች ለወያኔ/ኢህአዴግ እውቅና ሰጥተዋል ሲሉ ተችተዋቸዋል።

አቶ በድሩ አደም ሰሞኑን ለሪፖርተር ጋዜጣ በሚሰጡት ቃለምልልስ ያለእኔ ፖለቲከኛ በዚህች ሀገር ላይ የለም እስከማለት የደረሱ ሲሆን፣ ሁሉንም ነገር "እኔ ብቻ ነኝ ትክክል" የሚል ምላሽ ሲሰጡ መስተዋላቸውን ቃለምልልሱን የተከታተሉ ሀገር ቤት የሚኖሩ ወገኖች ገልፀዋል።

ባሳለፍነው ዕሁድ በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በሰጡት ቃለምልልስ "ዲያስፖራው የሁለቱን ቡድን እንዴት ነበር የተቀበለው?" ተብለው ሲጠየቁ፣ "ህዝቡ ቅንጅት ለሁለት በመከፈሉ በጣም አዝኗል። መጀመሪያ የዶ/ር ብርሃኑን ቡድን አምኖ ነበር። በኋላ እውነቱን ሳስቀምጥላቸው በብዛት ተመልሰዋል። ተፀፅተዋል ..." ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

ስለወ/ት ብርቱካን ምርጫ ሲጠየቁም "... ያለምንም ልምድ ኦሮሞ ስለሆነችና ሴት ስለሆነች ዶ/ር ብርሃኑ እሷን ተጠቅሞ ልደቱን ከጣለ በኋላ፤ እሷን አሻንጉሊት በማድረግ ለመጫወት አስቦ ነው ..." ሲሉም መልስ ሰጥተዋል።

አቶ ተመስገን ዘውዴን በሚመለከትም "... ወ/ት ብርቱካን እንደ ጠላት ነበር የምትቆጥራቸው። እኔ አቶ ተመስገን ዘውዴ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆነ በፊትም እናገር ነበር ..." ሲሉም እሳቸው ሁሌ አዋቂ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ከኢ/ር ኃይሉ ሻውል ሌላ ሰው የለም ብለው ወራት ባላስቆጠረ ጊዜ ውስጥ ሲሰብኩ የነበሩት አቶ በድሩ አደም ዛሬ ደግሞ "በምንም ተዓምር ከዚህ በኋላ ከሳቸው ጋር አልሠራም" ሲሉ ተደምጠዋል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር ቃለምልልሱን ያነበቡ በሀገር ውስጥ ያሉ አስተያየት ሰጪዎችን ሲያነጋግር አብዛኞቹ "የወያኔን ጥሬ ስጋ በበሉበት አፋቸው 'ቅንጅት የጀመራቸውን ብዙ ነገሮች ኢህአዴግ ተግባራዊ እያደረገ ነው' ሲሉ ለወያኔ እውቅና ሰጥተዋል" ብለው አቶ በድሩ አደምን ተችተዋቸዋል።

አቶ በድሩ አደም የቅንጅት ከፍተኛ አመራሮች ይቅርታ ጠይቀው ሲፈቱ እሳቸው ይቅርታ ባለመጠየቃቸው ዘግይተው መፈታታቸው አይዘነጋም። በወቅቱ ከቃሊቲ እስር ቤት ተለቅቀው ሲወጡ በቀጥታ ወደቤታቸው ሳይሆን የሄዱት፣ ኢ/ር ኃይሉ ሻውል መኪናቸውን ልከውላቸው ወደ ኢ/ሩ ቤት ነበር ያመሩት። እዚያም ሄደው የኢንጂነሩን እግር አጎንብሰው ስመው እንደነበር የአዲስ አበባው ሪፖርተራችን የዓይን ምስክሮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

(ሰሞኑን በአዲስ አበባ ጋዜጦች የአቶ በድሩን የፖለቲካ አቋም አስመልክቶ "የሣምንቱ አስደንጋጭ ዝውውር" በሚል ርዕስ የወጣውን መጥፍ አስነብበኝ) 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ