Ethiopia Zare (አርብ ኅዳር 4 ቀን 2002 ዓ.ም. November 13, 2009)፦ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፕሬዝዳንት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዲቅሳን ለማስፈታት ፊርማ ማሰባሰብ ለመጀመር መንቀሳቀሱን ገለጸ።

 

ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የሰብዓዊ ጥሰት በተለያዩ ጊዜያት ይፋ በማውጣትና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግንዛቤ በመስጠት የሚታወቅ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ፣ የብሔሮች ግጭት፣ በሰብዓዊ አያያዝና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጉዳይ መግለጫ ሲያወጣ መቆየቱ ይታወቃል።

 

አምነስቲ ትናንት በድረ ገጹ እንዳስነበበው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ያለፍትህ ሂደት በእስር መቆየት እንዳሳሰበው ገልጾ፤ ከኅዳር 26 ቀን እስከ ታህሳስ 4 ቀን 2002 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ አደርጋለሁ ብሏል።

 

የዓለማቀፉ ማኅበረሰብም በፊርማ ማሰባሰቡ ተግባራዊነት አወንታዊ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊና ፍትሀዊ ሥርዓት እንዲገነባ የሚሹ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የፊርማ ማሰባሰቡ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።

 

ወ/ት ሚዲቅሳ ቃሊቲ እስር ቤት ከወረዱ የሚቀጥለው ወር ታህሳስ 4 ቀን አንደኛ ዓመታቸውን ያስቆጥራሉ።

http://www.amnesty.org/en/library/info/AFR25/008/2009/en

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ