Ethiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 7 ቀን 2002 ዓ.ም. November 16, 2009)፦ በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውና 44 ሜትር ጥልቀት ያለው የተከዜ ሃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት ባለፈው ሣምንት መጨረሻ መመረቁ ተገለጸ።

 

75 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው አራት ተርባይነሮች ያሉት ይኸው ሃይድሮ ፓወር የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እንደሚያቃልል የተነገረለት ሲሆን፣ ግዙፍና ከ300 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል ነው ተብሏል።

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከቻይናው ናሽናል ዋተር ሪሶስ ኤንድ ሃይድሮ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ጋር የተፈራረመው ከ7 ዓመት በፊት ሲሆን፤ በወቅቱ ከ5 ዓመታት በኋላ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ በጉጉት ሲጠበቅ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሊጓተት ችሏል።

 

የተከዜው የሃይድሮ ፕሮጀክት በተለይ በሰሜኑ አካባቢ ለሚገኙ ሀገራት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ