Ethiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 6 ቀን 2002 ዓ.ም. November 16, 2009)፦ 22 ፎቆች ያለው በኢትዮጵያ ትልቁ የናኒ ሕንፃ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ለተሰማሩ የሳውዲ ዐረቢያ ባለሀብቶች በነፃ እንደሚሰጥ ምንጮቻችን ጠቆሙ።

በሼኽ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ባለቤትነት የሚታወቀው ይኽው ሕንፃ ከተሰራ ጀምሮ ለረጅም ጊዜ ያለአገልግሎት የተቀመጠ ሲሆን፣ አሁን ግን ለሳውዲ ባለሀብቶቹ ይሰጣል ተብሏል።

 

ሕንፃው በሥራ ላይ ሳይውል የቀረው ባለሀብቱ ግዮን ሆቴልን በተጨማሪነት ለመግዛት ጠይቀው መንግሥት ፍላጎት ባለማሳየቱ አጥረውት ማስቀመጣቸው ይታወቃል።

 

ሳውዲ ዐረቢያውያኑ ኢንቨስተሮች ለእርሻ አገልግሎት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲጠቀሙበት በአዲስ አበባ ዋና ቢሯቸውን በናኒ ህንጻ እንዲያደርጉ መወሰኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል።

 

ሼክ አል-ዓሙዲ እስካሁን ካላቸው ኢንቨስትመንት በተጨማሪ 80 ሺህ ሔክታር መሬት መጠየቃቸውን ምንጮቹ አክለው፤ በባለቤትነት ያስገነቡት የናኒ ህንጻ ለሳውዲ ባለሀብቶች መንግሥት በነፃ ሰጥቷል ለተባለው መረጃ ምንም አይነት ምላሽ አልሰጡም።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ